፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 13 2017| NBC ETHIOPIA- በሲሪላንካ አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ኑራ ኩሙራ ዲሳናያኬ ቃለ መሀላ መፈጸማቸው ተገለጸ፡፡
ቃላ መሀላ በፈጸሙበት ወቅት፤ በሀገሪቱ የተከሰተውን የኢኮኖሚ መዋዠቅ እንደሚያስተካክሉ ተናግረዋል፡፡
የግራ ዘመም ፖለቲከኛው ዲሳናያኬ በሀገሪቱ ለረዥም ጊዜ ስር የሰደደውንና ሙስና እና ብለሹ አሰራረር ለማስወገድ እንደሚጥሩ ነው የገለጹት፡፡
ከፈረንጆቹ 2022 ወዲህ የመጀመሪያ ነው የተባለው ምርጫ የተካሄደው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጎታባያ ራጃፓካሳ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ነው ተብሏል፡፡
ተመራጩ ፕሬዝዳንት ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋላ አዲስ የፖለቲካ ባህልና ስልት ያስፈልገናል ለዚህ ደግሞ ቆራጥ እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል፡፡ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
በ – ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












