፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 10 2017| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ በጎርፍ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ከ1 ሚሊዮን 500 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው የፊኖ ዱቄትና ዘይት ድጋፍ ተደርጓል።
በኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር የአማራ ክልል ቅርንጫፍ የፕሮግራም ክፍል ባለሙያ አቶ አለበል ቢያድጌ፤ ማህበሩ ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በጎርፍ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ከ1 ሚሊዮን 500 ሺ ብር በላይ ግምት ያላቸው የፊኖ ዱቄትና ዘይት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል።
ማህበሩ ከፖለቲካ፣ ከሃይማኖት እና ከዘር የፀዳ ማህበር በመሆኑ ተሸከርካሪዎች በተለያዩ ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ ማህበረሰቡ ትብብር እንዲያደርግም ባለሙያው አሳስበዋል።
የፎገራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንድርያስ ማሩ በበኩላቸው፤ ቀይ መስቀል ማህበር በጦርነትና ሰው ሰራሽ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ የሚያደርግና ወገንተኝነቱ ለተጎዱ ማህበረሰቦች ነው ብለዋል፡፡
የድጋፉ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል አርሶ አደር ጋሻው ሞቴ፣ ከቅድስት ሃና፣ እና ወይዘሮ ጥሩወርቅ መሃሪ በሰጡት አስተያየት፤ በጎርፍ ምክንያት ሃብትና ንብረቶቻቸው ማጣታቸውን በመግለጽ ማህበሩ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የቀይ መስቀል ማህበሩ ከዚህ በፊት በፎገራ ወረዳ በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው 500 የቤተሰብ ሃላፊዎች 6 ሚሊየን 700 ሺ ብር የሚጠጋ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












