፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 10 2017| NBC ETHIOPIA- ዩክሬን በሩሲያ፣በኢራን፣በቻይና ኩባንያዎችና ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ መጣሏ ተሰምቷል፡፡
የዩክሬን የፀጥታና የመከላከያ ምክር ቤት በሶስቱ ሀገራት ስድስት ግለሰቦችና ከአርባ በላይ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ያቀረበውን የውሳኔ ረቂቅ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ማፅደቃቸው ነው የተሰማው፡፡
ይህንኑ ዩክሬን የጣላቸውን ማዕቀብ በማስፈፀሙ በኩል የሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክርቤት የሀገሪቱ የፀጥታና የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ ብርቱ ሀላፊነት እንደተጣለባቸው ነው የተገለፀው፡፡
ዩክሬን በሶስቱ ሀገራት ግለሰቦችና ኩባንያዎች ላይ ስለጣለችባቸው ማዕቀብ ለአውሮፓ ህብረት ለአሜሪካና ለሌሎች ሀገራት ማሳወቅ እንደለባት ነው የተነገረው፡፡ ዘገባው የዩክሬን ፎርም ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












