፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 08 2017| NBC ETHIOPIA-በመላዋ ሊባኖስ እስራኤል ቀብረዋለች በተባለ የፈንጂ ጥቃት የሰዎች ህይወት መቀጠፉና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ሰዋች መቁሰላቸው ተነግሯል።
የሊባኖሱ ተዋጊ አንጃ ሄዝቦላ ክፉኛ ያማረረበትና የዘጠኝ ሰዎችን ህይወት ቀምቶ ከሁለት ሺ በላይ ክፉኛ ያቆሰለውን በየቦታው የተቀበረ ፈንጂ ጉዳይ የአጸፋ ምላሹ የከፋ ይሆናል ሲል ነው የዛተው።

የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እስራኤል ፈንጂዎቹን በሊባኖስ ምድር የቀበረቻቸው በሀገሪቱ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተቀጥረው በሚሰሩ ዜጎቿ በኩል እንደሆነ ነው ፍንጭ የሰጠው በሊባኖስ ስለደረሰው ፍንዳታ ከእስራኤል በኩል የወጣ መረጃ የለም።
በሊባኖስ ምድር ከፈነዳው ፈንጂና ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ደግሞ አንዱ በሊባኖስ የኢራኑ አምባሳደር ሞጅታባ አምኒ መሆናቸው ተገልጿል።
ፍንዳታውን ተከትሎም ሊባኖስ በመላ ሀገሪቱ ትምህርት እንዲዘጋ ማወጇን የበርናማ ዘገባ ያስረዳል።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












