፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 2 2016| NBC ETHIOPIA- የሪፎርም ቀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ተከብሯል።
ከንቲባ አዳነች ከተማ አስተዳደሩ የሪፎርም ስራ ካከናወነባቸው ተቋማት መካከል ኤጀንሲው አንደኛው መሆኑን ገልፀው በቀጣይም የሪፎርም ስራው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ባለፈው አመት 16 ተቋማትን ሪፎርም ማድረግ መቻሉን የተናገሩት ከንቲባዋ በዚህም ውጤቶች መገኘታቸውን አንስተዋል።
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና አስኪያጅ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው ነዋሪዎች መታወቂያቸው መዘጋጀቱን ቤታቸው ሆነው የሚከታተሉበት አሰራር ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆኑን ገልፀዋል።












