፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA- ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከተሞችን ማዘመን እና ለነዋሪዎች ምቹ ማድረግ እንደ አህጉር የጋራ እቅዳችን በመሆኑ በአንድነት እንሰራለን ብለዋል።
ከተሞችን የማስፋፋት ስራም አፍሪካውያን በራሳችን መፍትሔ ማስቀመጥ እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ሰላም እና እድገት በአፍሪካ እንዲረጋገጥ የከተማነት ስራ ቁልፍ መሠረት መሆኑን አንስተው ለነገዋ አፍሪካ በሕብረት እንስራ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












