Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

“ከመስከረም እስከ ህዳር ያሉ ሶስት ወራቶች ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ የሆኑ ወራቶች በመሆናቸው ማህበረሰቡ ራሱን ሊጠብቅ ይገባል” -ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)

September 3, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨   

አዲስ አበባ | ነሐሴ 28 2016| NBC ETHIOPIA- በ2023 ዓ/ም የወባ በሽታን ለማጥፋት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ ክልል ዓቀፍ የወባ ሳምንት ዘመቻ በባህር ዳር በይፋ ተጀምሯል፡፡

የዘመቻውን መጀመር ይፋ ያደረጉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማሕበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አንስተው ሰማንያ በመቶ የክልሉ አካባቢዎች ለበሽታው ስርጭት አመቺ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከመስከረም እስከ ህዳር ያሉ ሶስት ወራቶች ለወባ በሽታ ስርጭት አመቺ የሆኑ ወራቶች መሆናቸውን ጠቁመው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በልዩ ትኩረት በመስራት በሽታው በማህበረሰቡ ላይ ሊያደርስ ከሚችለው የከፋ ጉዳት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአብክመ ጤና ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በ2017 ዓ/ም በጤናው ሴክተር በትኩረት ከሚሰሩ ዘጠኝ መሰረታዊ ግቦች ውስጥ የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ባለፉት አምስት ዓመታት የወባ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በበጀት ዓመቱ 1.5 ሚሊዬን ህዝብ በወባ በሽታ መያዙን የገለጹት ሃላፊው መከላከያ መንገዱን የጠቆሙ ሲሆን የማህበረሰቡን ግንዛቤ በመጨመር፣ ለትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን በማፅዳት፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስና በማዳረቅ፣ ኬሚካሎችን በመርጨትና የአልጋ አጎበሮችን በአግባቡና ዘወትር በመጠቀም መከላከል እንደሚቻል ተናግረዋል።

አጎበሮችን ለአላስፈላጊ አገልግሎቶች ከመጠቀም መቆጠብ ይገባል ያሉት አቶ አብዱልከሪም እንደ ክልል ያለውን የወባ በሽታ ስርጭት ለማስወገድ የሚረዱ ተግባራትን ተኩረት ሰጥቶ በመስራት የህዝብን ጤና መጠበቅ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ወባን ለማጥፋት የተሰሩ ውጤታማ ስራዎችን በተሻለ ማስቀጠል እንደሚገባ የጠቀሱት ቢሮ ሃላፊው ወባ ከሚከሰትባቸው ጊዜያት ቀደም ተብሎ የጥንቃቄ ስራዎችን በመስራት ወባን ለማጥፋት መረባረብ ተገቢ መሆኑን አሳስበዋል።

የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ በበኩላቸው የወባ በሽታ ትኩረት የሚፈልግ ከመሆኑ ባሻገር ማህበረሰቡ ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን በማጽዳት ራሱን ከበሽታ መጠበቅ እንዳለበት አንስተዋል።

አቶ በላይ አያይዘውም በአማራ ክልል ያለው ወቅታዊ ሁኔታና የመንገዶች መዘጋጋት የወባ ሥራ ቁጥጥርን አዳክሞታል ያሉ ሲሆን ህብረተሰቡ ወባን ለመከላከል ያለው ዝቅተና ግንዛቤና ቸልተኝነት ሌላው ምክንያት እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

“ወባ የማህበረሰብ ችግር እንዳይሆን እናድርግ!” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የወባ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ የክልል ቢሮ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ አጋር ድርጅቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል መረጃው የአማራ ክልል ጠና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ነዉ፡፡

📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

📌Website – https://nbcethiopia.com/news/

📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

አብዮተኛው ቭላድሚር ሌኒን

Next Post

የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የፋይናንስ አካታችነት ስራዎችን እንደሚደግፍ ገለጸ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የፋይናንስ አካታችነት ስራዎችን እንደሚደግፍ ገለጸ

የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የፋይናንስ አካታችነት ስራዎችን እንደሚደግፍ ገለጸ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስመራ ያለውን ገንዘብ እንዳያንቀሳቅስ መከልከሉን ገለፀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስመራ ያለውን ገንዘብ እንዳያንቀሳቅስ መከልከሉን ገለፀ

የመጀመርያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም እየተካሄደ ነው

የመጀመርያው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም እየተካሄደ ነው

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?