መላዋ ዩክሬን በሩሲያ የአየር ጥቃት ስትደበደብ የጎረቤቷና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት አባል ሀገሯ ፖላንድም የራሷንና የጥምረቱን አየር ኃይል የአየር ክልሏ እንዳይደፈር ማጠናከሯ ነው የተሰማው፡፡
ሩሲያ የዩክሬኗን ዋና ከተማ ኪቭን ያደባየቻት በበርካታ ሚሳይሎች ጥቃት ሲሆን የከተማዋ ፍርስራሽ ያቆሰላቸውንና በጥቃቱ የተጎዱትን ለማሰባሰብ ከሀገሪቱ መንግስት የተሳማሩ ሀይሎች መኖራቸው ነው የተገለፀው፡፡

ሩሲያ በሚሳይሎቿ የከፋ ጥቃት ብትፈፅምም የዩክሬን አየር መከላከያዎች ግን በጥቃቱ ልክ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ መከላከላቸውን የ ዘ ቴሌ ግራፍ ኦንላይን ዘገባ ይስረዳል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ












