፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 23 2016| NBC ETHIOPIA-አለም አቀፍ ተቀባይነትን ያተረፉ የበረራ ላይ ህግና ደንቦችን ያረቀቀው የአሜሪካን ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ከፈረንጆቹ አቆጣጠር 2018 ጀምሮ በአውሮፕላን በረራ ወቅት የማይገባ እና በህግ የተከለከሉ ድርጊቶችን የሚከውኑ መንገደኞች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ስለመምጣቱ በአሃዝ የተደገፈ መረጃን ይፋ አድርጓል፡፡
የአውሮፕላን በረራ የሚያደርጉ መንገደኞች አደንዛዥ እጾችን መጠቀም ከበረራ መከልከልን የሚያስከትል ትልቅ ጥፋት ነው፣የደህንነት መመሪያዎችን እንደ የደህንነት ቀበቶ ማሰር፣ ሲጋራ ማጨስ፣ ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ማጥፋት ከበረራ በፊት በደንበኞች የሚተገበው ጥብቅ ትእዛዝ ሲሆን በበረራ ሰራተኞች የሚነገሩ የደህንነት ማስታወቂያዎችን መከታተል እና መፈጸም ደግሞ ከሁሉ የላቀ የአየር ትራንስፖርት መመሪያ ነው፡፡
ከበረራ ሰራተኞች ጋር አሊያም ከሌሎች ተሳፋሪዎች ጋር የቃል ግጭት መፍጠር በበረራ ወቅት ፍጹም የተለከለከሉ ድርጊቶች ናቸው የሚለው የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር እነዚህን ጥብቅ ክልከላዎች የሚፈጽሙ መንገደኞች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሷል፡፡
በዓለም ላይ ከሚደረጉ በረራዎች መካከል ቢያንስ የሶስት ሰዓታት ውስጥ አንዴ ጨዋነት የጎደለው ተግባርን አሊያም ከላይ የተጠቀሱ ጥብቅ የበረራ ህጎችን የሚጥሱ መንገደኞች አሉ የሚለው መረጃው ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 70 በመቶ የሚሆኑት አንዳንድ ጥፋቶችን ያጠፋሉ፣ በወር ውስጥ ደግሞ አንድ ጊዜ ይህ የሕግ ጥሰት አውሮፕላኑ በድንገተኛ እንዲያርፍ አስገዳጅ የሚሆንበትን የደህንነት መመሪያ ጥሰት ይፈጸማል፡፡

ትእዛዛትን አንቀበልም በሚል የሚፈጸሙ ጥፋቶች በአውሮፕላኑ እና ተሳፋሪዎች ደህንነት ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አላቸው፣ ለበረራ አውሮፕላን ውስጥ የገባ መንገደኛ ለጠብ መጋበዝ አሊያም የትኛውንም የበረራ ደህንነት መልእክቶችን እምቢኝ ማለት አላስፈላጊ አደጋን መጋበዝ ነው በሚል በበርካታ አየር መንገዶች ላይ የተቀመጠ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡
ጠብ አጫሪ ባህሪ እና አልታዘዝም ባይነት ሰራተኞቹን ከስራቸው ያዘናጋቸዋል።በነገራችን ላይ በአለም ላይ ያሉ አየር መንገዶች የማይታዘዝ ባህሪ ያለው መንገደኛ ሲሉ የለዩዋቸው ባህሪያት የሁሉም በሚባል ደረጃ ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው፡፡
👉በበረራ ወቅት ወይም በፊት ከመጠን በላይ መጠጣት
👉በበረራ ወቅት ወይም በፊት መድሃኒቶችን መጠቀም ወይም ከአልኮል ጋር መቀላቀል
👉የሰራተኞች መመሪያዎችን አለመከተል
👉በቃልም ሆነ በአካል ጠበኛ መሆን
👉የካቢን ሠራተኞችን ከስራቸው ማሰናከል
ምንም እንኳን ከጠቅላላው የበረራ ሰዎች ብዛት አንፃር ያልተገራ ተሳፋሪዎች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም፣ ድርጊታቸው የሚያሳድረው ተፅዕኖ በበረራ አኳኋን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በደህንነቱ ላይ ያልተመጣጠነ ተጽእኖ ይኖረዋል።
ከባድ የመንገደኞች ባህሪ መጨመር ለአቪዬሽን ማህበረሰብ እና በተለይም ለአየር መንገድ ትልቅ ስጋት ነው።ማንኛውም ተሳፋሪ እና የካቢን ሰራተኛ አባል ከአደጋ እና ከአደጋ ነፃ የሆነ በረራ የማግኘት መብት አለው። ጉዞ ተሳፋሪዎች እርስበርስ እና የካቢኔ ሰራተኞች በሚገባቸው አክብሮት የሚስተናገዱበት አስደሳች ተሞክሮ መሆንም አለበት።

መንገደኛ ሁሉ የራሱ የሆነ አሉታዊ አመለካከት ይኖረዋል፣ ከነዚህ ውስጥ በአቪዬሽን ላይ ስጋት ሊፈጥሩ ይችላሉ በተለይ በበረራ ወቅት አስፈላጊ ከሆኑ መልካም ባህሪ ጋር ተቃራኒ እና ሊግባባ የማይችል ከሆነ፡፡
ሌላው የአቪዬሽ ዘርፉ መንገደኞች ሊኖራቸው ይገባል ሲል የሚተማመንበት የራሱ የሆነ ባህሪ ያለው ዘርፍ ነው፡፡ ለምሳሌ “ምን ማድረግ እንዳለብኝ አትንገረኝም ማለት!” ይህን የሚል ግትርነት ባህሪ እና ተጋላጭነት የሚጋብዝ “ይህ በእኔ ላይ ሊደርስ አይችልም!” ወይም “ከዚህ በላይ የሚመጣ ምንም ነገር የለም የሚሉ ባህሪያት እጅግ አደገኛ ስለመሆናቸው በመግለጽ ከዚህ በተቃራኒ ላሉ መልካም ስነ-ምግባሮች መንገደኞች ተገዢ መሆን ይጠበቃባቸዋል፡፡
አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር IATA ደግሞ ያልተገራ ሲል የሚጠቅሳቸው የአየር ተሳፋሪዎችን ጉዳይ እንዴት እየፈታ እንደሚገኝ በደህረገጹ አስፍሯል፡፡ በፈረንጆቹ 2014 ላይ 70ኛውን አጠቃላይ አመታዊ ጉባኤ ሳያካሂድ ነው IATA ኢንዱስትሪው ያልተገሩ ያላቸውን የመንገደኞች ባህሪ ለመግራት የሚያስችለውን መራሆች በመተዳደሪያ ደንቡ ያካተተው፡፡
IATA ከፍተኛ ደረጃ ያለው ሰነድ በማሳተም ከሁሉም የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የበለጠ አስደሳች የአየር ጉዞ እንዲኖር ለማስቻል ያልተገራ እና የሚረብሹ የተሳፋሪዎችን ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ መወሰድ ያለባቸውን ተግባራዊ እርምጃዎችን በመግለጽ ለመንግስታት ማሳሰቢያን ጨምሮ ሰነዱን ያቀረበው፡፡
IATA የቺካጎ ኮንቬንሽን ጨምሮ ሌሎች ሊተገበሩ የሚገቡ የስነ-ምግባር ደንቦችን ያካተተ አለም አቀፍ ህጎችን አጽድቋል፡፡የአየር ትራንስፖርት እንዲህ ባሉ ወጥ አለም አቀፍ መግባባትን በተላበሱ ስርዓቶች የሚያልፍ በመሆኑ የሀገራት የአየር መንገዶች ሁሉም ተመሳሳይ እና ለዘርፉ ተስማሚ የሆኑ መመሪያዎችን መንገደኞች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያሳስባሉ፡፡
በበረራ ወቅት የካቢን ክሩዎች የሚሰጧቸው ማሳሰቢያዎች፣ ፓይለቶች የሚያስተላልፏቸው መልእክቶች በመንገደኞች ተቀባይነት ሊኖራቸው እንጂ ይህ ለምን፣ እንዴት እና መሰል ጥያቄዎች አልፎም እሰጣ ገባዎች ፈጽሞ የተከለከሉ እና በርካታ እገዳዎችን የሚያስጥሉ ጥፋቶች መሆናቸው ነው በዚህ ዙሪያ የተጻፉ መረጃዎች የሚያትቱት፡፡
በመጨረሻም በአውሮፓ ህብረት የአቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ የተጀመረው #notonmyflight ዘመቻ በርካቶች ያልተገባ ባህሪይን የዘው ወደ አውሮፕላን የሚገቡ ሰዎችን ድርጊት የሚነቅፍ ዘመቻ ይፋ ተደርጎ በበርካቶች ተግባራዊ እየተደረገ ሲሆን፣ በዚህም ውጤት መኖሩን የገለጸው አለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር በራካቶች ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ የሚያበረታታው፡፡
በ-ቆንጂት ዘውዴ












