፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 22 2016| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ልዑካን ቡድን ከበርሊን ከተማ ሚቴ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱ በሁለቱ እህትማማች ከተሞች በወሳኝ ትብብር ጉዳዮች በተለይም በጤና፣ በትምህርት እና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ዘላቂ ትብብር መፍጠር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል::

የበርሊኗ ሚቴ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ስተፋኔ ረምልንገር በሁለቱ ከተሞች በጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ አፅንኦት በመስጠት እርስ በእርስ ልምድ መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል::ከንቲባዋ የቤርሊኗ ሚቴ ከተማ ልምዷን ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን በመግለፅ በአዲስ አበባ ከተማ ለተሰጣቸው ማብራሪያ አመስግነዋል::
የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ ልዑካንን የመሩት ዶ/ር አሻግሬ ገብረወልድ አዲስ አበባ ከተማ ለአለም ከተሞች እድገት የምታጋራው ልዩ ገፅታ እንዳላት ያስታወቁ ሲሆን በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ ኮሚቴ ከከተማዋ ለመማር ያለውን ጉጉትም አስታውቀዋል::

ልዑካን ቡድኑ ከሚቴ ከንቲባ ርምልንግር እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር በመሆን በቻንስለር እና የሀገርቷ ፓርላማ ፊት ለፊት የተተከሉ ዛፎችን ጉብኝተዋል።
ልዑኩ በተጨማሪም የጎልማሶች እና መዋዕለ ህፃናት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን መጎብኘታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












