፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ብዙዎች የአለም የስነጥበብ መዲና እንዲሁም የውበት ተምሳሌት ሲሉ ያሞካሿታል። የዓለማችን ግዙፉ እና አስደናቂው ባለ ቀይ ጉልላት ካቴድራል መገኛም ናት የጣልያኗ እንቁ ፍሎረንስ ከተማ
እጅግ ጥንታዊ በሆኑት ታሪካዊ ማዕከሎች ፣ በታዋቂ ሙዚየሞች ፣ በአስደናቂ ኪነ ህንጻዎች ፣የጥበብ ጋለሪዎችን ፣ ሀውልቶች እና ልዩ ባህላዊ ቅርሶችን ይበልጥኑ ትታወቃለች።
ፍሎረንስ በማዕከላዊ ጣሊያን የምትገኝ የቱስካኒ ክልል ውስጥ የምትገኝ ከተማ ስትሆን የጣሊያን ስምንተኛዋ ትልቅ ከተማ ነች። ከ 712 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርባት፡፡

ከተማዋ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶችን ትስባለች። በጎርጎሮሳውያኑ 1982 የፍሎረንስ ታሪካዊ ማእከል በዩኔስኮ የአለም ቅርስ ተመዝገቧል።ፍሎረንስ በጣሊያን ፋሽን ውስጥ ትልቅ ሚና ስትጫወት ቆይታለች ። ከአለም አቀፍ 15 ምርጥ የፋሽን ዋና ከተማዎች ውስጥም ትመደባለች ።
አሁን ላይ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ተወዳጁ የጉቺ ብራንድ የተመሰረተው በፍሎረንስ ከተማ ሲሆን ተወዳጅ የሙዚቃ መሳሪያ ፒያኖ የትውልድ ቦታም ጭምር ናት ፍሎረንስ።ባርቶሎሜዮ ክሪስቶፎሪ በፈረንጆቹ በ1698 ፒያኖፎርት በመባል የሚታወቀውን ፒያኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ አስተዋውቋል።ፍሎረንስ ከሚገኙ በርካታ መዳረሻዎች መካከል በጥቂቱ እናስቃኛችሁ።
ለከተማይቱ የታሪክ ምስክር ስለመሆኑ ብዙዎች ይስማሙበታል። በፍሎረንስ እምብርት የሚገኝ ታዋቂ የቱሪስት መዳረሻ ነው። የፍሎረንስ ሳንታ ማሪያ ዴል
ፊዮሬ ካቴድራል

በፍሎረንስ በብዛት ከሚጎበኙ ምልክቶች አንዱ ነው። እናም ወደ ከተማዋ የሚጓዝ ማንኛውም ቱሪስት መጎብኘት ያለበት ድንቅ ስፍራ ነው።
ሳንታ ማሪያ ዴል ፊዮሬ ካቴድራል ግንባታው የተጀመረው በጎርጎሮሳውያኑ በ1296 በታዋቂው አርክቴክት እና ቀራጺ አርኖልፎ ዲ ካምቢዮ ሲሆን የተጠናቀቀው በ1436 ነው፡፡ ካቴድራሉን ሰርቶ ለማጠናቀቅም ወደ 140 ዓመታት ፈጅቷል። 153 ሜትር ርዝመት፣ 90 ሜትር ስፋት እና 90 ሜትር ከፍታ ያለው ካቴድራሉ በአማካይ እስከ 4.5 ሚሊዮን ጎብኝዎችን እንደሚያስተናግድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የኡፊዚ ጋለሪ በጣሊያን ፍሎረንስ የሚገኝ የጥበብ ሙዚየም ሲሆን በአለም ላይ በጣም ዝነኛ የጥበብ ስራዎች መገኛ ነው።የሰዕል ማሳያው በመጀመሪያ ዲዛይን የተደረገው እና የተገነባው እ.ኤ.አ በ1560 ነው። እ.ኤ.አ በ1769 ደግሞ ለሕዝብ ክፍት ተደረገዋል።

በየዓመቱ ወደ 1.9 ሚሊዮን የሚጠጉ ቱሪስቶች የኡፊዚ ጋለሪ ይጎበኛሉ።ይህም በዓለም ላይ በጣም ታዋቂ ከሚባሉት የሰዕል ጋላሪዎች አንዱ ያደርገዋል።
ሌላኛው የቱሪስቶች አይን ማረፊያ የሆነው ታዋቂው ፓላዞ ቬቺዮ ሙዚየም ነው።
በፍሎረንስ የሚገኘው ፓላዞ ቬቺዮ ወይንም “የድሮው ቤተመንግስት” ተብሎ የሚጠራው ሙዚየም የ14ኛው ክፍለ ዘመን ዝነኛ ቅርስ ነው።
ፓላዞ ቬቺዮ በፍሎረንስ ታሪክ ውስጥ አስፈላጊ መልክቶችን ለማስተላለፍ ደውል በመደወል ትልቅ ሚና ተጫውቷል። እንደ ዶናቴሎ፣ብሮንዚኖ እና ማይክል አንጄሎ ባሉ የጣሊያን ስመ ገናና አርቲስቶች የተሰሩ አስደናቂ የስነ ጥበብ ስራዎች እና ቅርጻ ቅርጾች፣ መገኛ ነው።
በ-ሀይማኖት ወርቁ












