፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 21 2016| NBC ETHIOPIA- በደብረ ብርሃን ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባጃጅ ተሽከርካሪን በመጠቀም በማህበረሰቡ ላይ ስርቆትን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን እየፈጸሙ የሚገኙ አካላት እንዳሉም የጸጥታው ምክር ቤት አመላክቷል።
በዚህ ወንጀል የተሠማሩ አካላት የባጃጅ ተሽከርካሪዎቹን ማሟላት ያለባቸውን ህጋዊ ሰውነት ተሽከርካሪዎቹ ሳያሟሉ እንደሚያሽከረክሩም የጸጥታው ምክር ቤት እንደደረሰባቸው አንስቷል።
ለህዝብ ሰላም ሲባል የጸጥታ ምክር ቤቱ ህግና ስርአት ለማስከበር ያመች ዘንድ ማንኛውም የባጃጅ አሽከርካሪ በተሽከርካሪው ላይ ስቲከር መለጠፍ ፣ መጋረጃ መጠቀም እንደማይቻል በክልከላው ገልጿል። ያለስምሪት ፣ የጎን ቁጥርና ታርጋ ሳይጠቀሙም ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።
ከዛሬ 4:00 ጀምሮ የባጃጅ ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ ማሽከርከር እንደሚቻል የጸጥታ ምክር ቤት ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ሰአት ውጭ ወይም ከላይ መደረግ ያለባቸውን ያላሟላ ባጃጅ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ በባጃጅ አሽከርካሪውና ባለንብረቱ ላይ እንደሚወሰድ ምክር ቤቱ አመላክቷል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












