፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 21 2016| NBC ETHIOPIA- በአዲስ አበባ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረሪ እንዲሁም በድሬዳዋ የተደረገው የሃገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍን በአማራ ክልል ለማካሄድ መሰረት ነው ያለውን የተባባሪ አካላት ስልጠና ማካሄዱን የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልጿል።
ነፍጥ አንግበው ጫካ የገቡ ታጣቂዎች ዋስትና ተሰጥቷቸው በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀው ኮሚሽኑ አሁንም ይህን ከማድረግ አልቦዘንኩም ብሏል።
የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በሲዳማ ክልል ነሀሴ 22 ይጀምራል።

ከነገ ነሀሴ 22 ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው የምክክር ምዕራፍ የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የማህበረሰብ ወኪሎች፣ የሶስቱ የመንግስት አካላት ተወካዮች፣ የተቋማትና ማህበራት ተወካዮች እና የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች የሚሳተፉበት ነው።

ከ1800 በላይ እንደሚሆኑ የተገለፁት እነኚህ ተወካዮች ከወከሉት ማህበረሰብ የሰበሰቧቸውን ሀገራዊ መግባባት ሊደረስባቸው ይገባል የሚሏቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መክረው ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደሚያስረክቡ ይጠበቃል።
በነገው እለት የሚጀመረውን የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ አስመልክቶ ኮሚሽኑ መግለጫ ተሰጥቷል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












