፨ ፨ ፨ ፨ ፨ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ በትወና በመድረክ ቴአትሮች፣ በዳይሬክትንግ፣ በሬዲዮ ድራማዎች ፣ የቴሌቪዥን ድራማዎች በበርካታ የጥበብ ስራዎች ላይ ባለፉት 35 አመታት ከትወና እስከ ዝግጅት ሙያዊ አደራውን በሚገባ የተወጣ አርቲስት ነው፡፡ አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ ባለትዳር እና የሁለት ወንዶች እና አንዲት ሴት ልጆች አባት ነው። ኤንቢሲ አትዮጵያ ለቤተሰቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል