፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 15 2016| NBC ETHIOPIA-ታይዋን ደሴት ከጃፓን ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመመሰረት እንደምትሻ አስታውቃለች፡፡
የታይዋን ፕሬዝዳንት ላይ ቺንግቴ ከጃፓኑ የሊበራ ዴሞክራቲክ ፓርቲ የወጣቶች ክፍል መሪው ሱዙኪ ታካኮ ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደተናገሩት የታይዋን ደሴትና ጃፓን በጋራና በፅናት ቆመው የአምባገነኑን የቻይና መንግስት መዋጋት አለባቸው ነው ያሉት፡፡
በጃፓኑ የወጣቶች ክፍል ሀላፊ ሱዙኪ ታካኮ የሚመራውንና ከሰባ በላይ አባላት ያሉትን የጃፓን የልዕካን ቡድን በፕሬዝዳንታዊ ጽ/ቤት ተቀብለው ያናገሩት፡፡
የታይዋን ደሴት ፕሬዝዳንት የቻይናን አቋም ለማስቀየር ከተፈለገ የቀጠናው ሀገራት በተለይም ታይዋንና ጃፓን ትብብራቸውን ማጠናከር ብቸኛው ምርጫቸው ነው ሲሉ አስምረውበታል፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












