፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 03 2016| NBC ETHIOPIA- የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተገበራቸው ያሉ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ጥያቄዋ በፍጥነት መልስ እንዲያገኝ እንደሚያግዝ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ከአለም የንግድ ድርጅት አክሴሽን ዲቪዥን ዋና ዳይሬክተር ማይካ ኦሺካዋ ጋር በአገሪቱ የአለም የንግድ ድርጅት አባልነት የድርደር ሂደት ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበች ረዥም ጊዜ ያስቆጠረች ሲሆን መንግስት በአሁኑ ወቅት እየተገበራቸው ያሉ በርካታ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የድርድር ሂደቱን በፍጥነት ለማጠናቀቅ እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ለሚካሄደው 5ኛው የስራ ቡድን ስብሰባ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች ወደ ተግባር የገቡ በርካታ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ያካተተ እንዲሆን ከድርጅቱ ባለሙያዎች ጋር ሰነድ በመከለስ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ሚኒስትሩ አብራረተዋል፡፡
የአለም የንግድ ድርጅት አክሴሽን ዲቪዥን ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄን ካጓተቱ ምክንያቶች መካከል በቅርቡ ተግባራዊ መሆን የጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው ማሻሻያው የድርድር ሂደቱን እንደሚያፋጥን እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

አያይዘው የዓለም ንግድ ድርጅት ያለ ኢትዮጵያ ተሳትፎ ሙሉ አይሆንም ያሉት ዳይሬክተሯ ድርድሩን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ ድርጅቱ ቴክኒካል ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚሰጥል መግለጻቸውን ከሚስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












