የኖቤል ሽልማት አሸናፊው ሙሀመድ ዩኑስ ናቸው በባንግላዴሽ የሽግግር መንግስቱ መሪ ሆነው የተመረጡት ፡፡
ዩኑስ የሽግግር መንግስቱ የበላይ ሆነው የተመረጡት በሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሻሃቡዲን እና በተማሪዎች የፀረ አንድነት ንቅናቄ አስተባባሪዎች መካከል በተደረገው ውይይት ነው፡፡

ሰሞኑን ከስልጣናቸው የለቀቁት የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚስትር ሼክ ሀሲናን ከሀገር መኮብለል ተከትሎ አስራ ሶስት አባላት ያሉት የፀረ አንድነት ንቅናቄ ቡድን ወደ ዋና ከተማዋ ዳካ ተጉዞ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መምከሩ ይታወቃል፡፡
በተማሪዎች የሚመራው የባንግላዲሽ የተቃውሞ እርምጃ በዋናነት የመንግስትን ስራ በኮታ ለመስራት የወጣውን ህግ ማውገዙ ይታወቃል ዘገባው የአኒ ኒውስ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ












