፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 02 2016| NBC ETHIOPIA- የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሐምሌ ወር ብቻ 26 ሺህ 195 ዜጎች ሰልጥነው ወደተለያዩ መዳረሻ ሃገራት ለስራ መሰማራታቸውን ገለጹ።
ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የሚኒስቴሩን የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ገልጸዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተገኙ ልምዶችን በመውሰድ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የራሳቸውን ሚና በአግባቡ በመለየትና በማቀድ ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል።

የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ቀደም ሲል ከነበረው የመካከለኛ ምስራቅ መዳረሻ በተጨማሪ ወደ አውሮፓ ሃገራት መላክ መጀመሩ በወሩ ከተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎች ውስጥ መሆኑን ተመልክተናል ሲሉም ገልጸወል።
አገልግሎት አሰጣጡም ፍትሃዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም አጠቃላይ ስምሪቱ የዜጎችን መብትና ደህንነት ያስጠበቀ እንዲሆን በማድረግ በሐምሌ ወር 26 ሺህ 195 ዜጎችን አሰልጥኖ ለሥራ ማሰማራት መቻሉን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከር በባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ ሥራ ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገርና ዓለም አቀፍ የሥራ ገበያው የሚያመጣውን ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም የማሰልጠኛ ተቋሞቻችንን በአግባቡ አደራጅቶ ጥራት ያለው ስልጠና እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ ተግባብተናል ብለዋል።
አምባሳደር ግርማ ብሩ ሥራውን በቅርበት በመከታተልና በመደገፍ በዘርፉ እያበረከቱ ላለው ትልቅ አስተዋጽኦ እንዲሁም ሚናችሁን እየተወጣችሁ ላላችሁ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ምስጋናዬ የላቀ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












