፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 27 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አመራሮች እና ሰራተኞች በቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ- ግብር አካሂደዋል።
የዘንድሮው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር “የምትተክል ሀገር፤ የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከናወነ ይገኛል።

ባንኩ በዘንድሮው መርኃ ግብር በአዲስ አበባ ማዕከል ብቻ ከ50 ሺህ በላይ ለምግብነት የሚውሉ፣ ሀገር በቀል ችግኞችን ለመትከል አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ከአዲስ አበባ ማዕከል በተጨማሪ በሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 23 ዲስትሪክቶች የችግኝ ተከላው እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በ-ሀይማኖት ወርቁ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












