፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 26 2016| NBC ETHIOPIA- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራን ለመተግበር ዕቅድን በሀላፊነት ወደ መሬት ማውረድ ይገባል አሉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ዛሬ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ኦረንቴሽን ውይይት ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

መነሻን አውቆ፣ መድረሻን ተረድቶ ለመስራት ዕቅድ መሰረታዊ ነገር ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ ክልሉን ከነበረበት ሁኔታ የሚያሻግር፣ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራን ዕውን ለማድረግ የተዘጋጀውን ዕቅድ በሃላፊነትና በጋራ ተናቦ መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በመሆኑም የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥና አሻጋሪ ልማቶችን በውጤት ለመፈጸም የአመራሩ ቅርጠኝነትና ዲስፕሊን ወሳኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












