፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 19 2016| NBC ETHIOPIA- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተካሄደ በሚገኘው የአጀንዳ ማሰባሰቢያ ከክልሉ የተውጣጡ የማህበረሰቦች ክፍሎች ለሀገራዊ ምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች እየመረጡ ነው።
የማህበረሰቡ ተወካዮች በትናንትናው ዕለት አጀንዳዎቻቸውን አቅርበዋል።በዛሬው መርሃግብርም ለሀገራዊ ምክክሩ ጉባኤ የሚሳተፉ የማህበረሰብ ወኪሎቻቸውን በመምረጥ ላይ ይገኛሉ።


ከክልሉ የተዉጣጡት 450 ማህበረሰብ ተውካዮቹ ከ3ዞን ከ27 ወረዳዎች የተሰባሰቡ ናቸው።
በቀጣዮቹ ቀናትም የክልሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ፣ፖለቲካ ፖርቲ ተወካዮች እና ባለድሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን የሚያቀረቡ ይሆናል።
በ-ሰላም ይልማ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











