፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 18 2016| NBC ETHIOPIA-አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአመቱ መጨረሻ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት አንዱ የሆነዉን የክረምት የበጎ አድራጎት መርሃግብር አስጀመረ።
ሆስፒታሉ በክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከሶስት መቶ በላይ ለሚደርሱ ህሙማን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት፣ እንዲሁም በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ህሙማን መርጃና የአረጋዉያን ማቆያ የስነ አዕምሮ ህክምና ለመስጠትና የቅድመ በሽታ መከላከል ለማድረግ አቅዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ ጤና ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በተለይም ከጤና ሳይንስ ኮሌጁ ጋር በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዉ አሁንም መከላከል ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ ተናግዋል። ጤና ባለሙያዎች እያበረከቱት ላሉት አስተዋፅኦም ምስጋና አቅርበዋል።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን ከ20ሺ በላይ ሰዎች በአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
በ-ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












