፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በፈረንጆቹ ሰኔ እና ሀምሌ ወር ተለቀው ከፍተኛ ገቢን በማስገባት በቦክስ አፊስ የፊልም ሰንጠረዥ የቀዳሚነት ደረጃን ካገኙ ፊልሞች መካከል ጥቂቶቹን እንንገራችሁ፡፡
Despicable Me 4
በፈረንጆቹ ሀምሌ 3 2024 ነበር ለእይታ የበቃው፡፡በክሪስ ሬኖድ እና በፓትሪክ ዴላጅ ዳይሬክት የተደረገው ፊልሙ ዲስፒኬብል ሚ ፤ ዲስፒኬብል ሚ 2 ፤ ሚኒየንስ ዘ ራይዝ ኦፍ ግሩ የተሰኙ የቀደሙ ክፍሎች አሉት፡፡

ቤተሰቡን የተቀላቀለው ትንሹ ግሩ በሚፈጥራቸው ሁነቶች ላይ የሚያተኩረው ፊልሙ አዝናኝ የአኒሜሽን ዘውግን ተላብሷል፡፡
100 ሚሊየን ዶላር ወጪ በማድረግ የተሰራው ፊልሙ ለእይታ ከቀረበበት እለት አንስቶ በመላው አለም ከ453 ሚሊዮን ዶላር በላይ በመሰብሰብብ ተወዳጅ በመሆን በቦክስ ኦፊስ የፊልም ሰንጠረዥ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
Bad Boys Ride or Die
በ Bilall Fallah እና Adil El Arbi ዳይሬክት የተደረገው ፊልሙ በድርጊት የተሞላ አስቂኝ ፊልም ነው፡፡

ፊልሙ በዋነኝነት ሁለት ፖሊስ ጓደኛሞች ከአደንዛዥ እፅ ዝውውር ጋር የተያያዘን ወንጀል ምርመራ ሂደት ላይ በሚያጋጥሟቸው ሁነቶች ላይ ሚያጠነጥን ነው፡፡ዊሊስሚዝ እና ማርቲን ላውረንስ በዋና ገጸ ባህሪያት በመላበስ እንዲም ሌሎች እውቅ ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡
በ130 ሚሊየን ዶላር በጀት የተሰራው ፊልሙ በፈረንጆቹ ሰኔ 7 2024 ነበር ለእይታ የቀረበው፡፡
ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ተወዳጅነትን በማግኘት በቦክስ ኦፊስ ቀዳሚ የደረጃ ሰንጠረዥ ለተከታታይ ሳምንታት ሲመራ የቆየው ፊልሙ ከ 370 ሚሊየን ዶላር በላይ ማስገባትም ችሏል፡፡
Fly Me To The Moon
በፈረንጆቹ 2024 ሀምሌ 12 ቀን ነበር ለእይታ የበቃው ፍላይ ሚ ቱ ዘ ሙን!
ቻኒንግ ታተም እና ስካርሌር ጆንሰን በዋና ገጸ ባህሪነት የተሳተፉበት ፊልሙ የአንድ ሰአት ከ32 ደቂቃ ርዝማኔ አለው፡፡

በማርኬቲን ባለሞያ እና የናሳ ዳይሬክተር በሆኑ ሁለት ጥንዶች የፍቅር ህይወት ላይ የሚጠነጥን ፍቅር ፊልም ነው፡፡ፊልሙን ሰርቶ ለመጨረሰ 100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፈጅቷል፡፡
Inside Out 2
በኬልሲ ማን ዳይሬክት የተደረገ ሲሆን የ1 ሰአት ከ 36 ደቂቃ የስክሪን ቆይታ ያለውበ2015 የተለቀቀው Inside Out ቀጣይ ክፍል የሆነው ፊልሙ የ13 አመት ታዳጊዋ ኬይሊ በሀይስኩል የትምህርት ቤት ቆይታዋ ስለሚያጋጥሟት የስሜት መለዋወጦች ላይ ያጠነጥናል፡፡

በ175 ሚሊየን ዶላር የተሰራው ፊልሙ በተለቀቀ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ 1 ቢሊየን 389 ሚሊየን ዶላር በላይ ማስገባት የቻለ ሲሆን እስካሁን ድረስ የቦክስ ኦፊስ የፊል ሰንጠረዥ በ 1ኝነት እየመራ ይገኛል፡፡
A Quiet Place: Day One
በፈረንጆቹ ሰኔ 27 2024 ለእይታ የበቃው A Quiet Place: Day One በ ሰኔ እና ሀምሌ ወር ተለቀው ተወዳጅነት ካገኙ እና የቦክስ ኦፊስ የፊልም ሰንጠረዥን በቀዳሚነት ከተቆጣጠሩ ፊልሞች ሌላኛው ነው፤

1ሰአት ከ 39 ደቂቃ የስክሪን ላይ ቆይታ ያለው ፊልሙ ሳም የተሰኘች መስማት የተሳናት ወጣት በኤሊያኖች በተወረረ ኒዮርክ ከተማ ውስጥ እራሷን አግኝታ ለማምለጥ የምታረጋቸውን ሁነቶች ያስመለክታል፡፡
190 ሚሊየን ዶላር ወጪ ተደርጎበት የተሰራው ፊልሙ ከተለቀቀ ዕለት ጀምሮ ከ 220 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢን ማስገባት የቻለ ተወዳጅ ፊልም ነው፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












