፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 15 2016| NBC ETHIOPIA-የአራተኛው ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ቅድመ ጉባኤ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ እና ሌሎች ታዳሚዎች ተገኝተዋል።
የዛሬው ኮንፍረንስ እ.ኤ.አ ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 3/2025 በስፔን ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ለልማት ጉባኤ የተዘጋጀ የቅድመ ጉባኤ መድረክ ነው።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ላይ በጂኦ ፖለቲካ ልዩነት ላይ የተመሰረተ ኢ-ፍትሐዊ የፋይናንስ ፍሰት ችግር ተፈጥሯል ብለዋል።
በቀጣይ ዓመት የሚደረገው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ጉባኤ ይህን የተዛባ የፋይናንስ ስርዓት መስመር እንደሚያሲይዝ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ዋና ፀሐፊው በስፔን የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ንግድና ኢንቨስትመንትን በማጠናከር የተሳለጠ የፋይናንስ ስርዓት ለመዘርጋት የጎላ አበርክቶ ይኖረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












