፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 10 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የበረራ ቲኬት ሽያጭ አገልግሎቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ መንገደኞቹ የሚሰጣቸው ዓለም አቀፍ የበረራ ቲኬት ሽያጭ አገልግሎቶች በሙሉ በውጪ ምንዛሪ (hard currency) ብቻ እንደሚሆን ተደርጎ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች ሲዘዋወር መመልከቱን ገልጿል፡፡
ይሁን እንጂ የጉዳዩ ትክክለኛ መረጃ በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀም መመርያ ማውጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ ቀደም ከሀገር ውጪ ተነስተው ወደ ኢትዮጵያ ለሚደረጉ ጉዞዎች በሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘብ ሲሰጥ የነበረውን የበረራ ቲኬት ሽያጭ አሰራር ከሐምሌ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል የተከለከለ መሆኑን እና በውጪ ምንዛሪ አገልግሎቱን የሚያገኙ መሆኑን ገልጿል።
ይኸውም ሀገር ውስጥ በሚንቀሳቀሱ በሁሉም አየር መንገዶች ተግባራዊ እንዲደረግ የወረደ መመርያ መሆኑን ያሳሰበ ሲሆን ኢትዮጵያዊያን እና ህጋዊ ሰነድ ያላቸው (የመኖርያ ፈቃድ፣ ቢጫ ካርድ፣ የሥራ ፈቃድ፣ የዲፕሎማቲክ ፈቃድ ወዘተ) የውጪ ሀገር ዜጎች በሙሉ ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሀገራት ለሚደረጉ በረራዎች የቲኬት ሽያጭ አገልግሎትን ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር መሰረት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል። ነገር ግን ትኬታቸውን በኢትዮጵያ የሚገዙ የውጭ ሀገር ዜጎች በውጭ ምንዛሬ መክፈል ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ እባክዎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የትኬት ሽያጭ ቢሮዎቻችንን በመጎብኘት፣ የጉዞ ወኪሎችን በማነጋገር ወይም ሀገር ውስጥ ከሆኑ ወደ 6787 በመደወል ዓለም አቀፍ የደንበኞች ማስተናገጃ ማዕከላትን እንዲያነጋግሩ ወይም የአየር መነገዱ ድረ ገጽ ላይ ካሉት ቁጥሮች በመምረጥ መደወል እንሰሚችሎ አስታውቋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












