Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የቱሪስት መዳረሻዋ-ታጂኪስታን

July 15, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሐምሌ 08 2016| NBC ETHIOPIA- መገኛዋ በማዕከላዊ እስያ ሲሆን ኡዝቤኪስታን፣ ኪርጊስታን፣ ቻይና እና አፍጋኒስታን የሚያዋስኗት ሀገራት ናቸው ታጂኪስታን

ታጂኪስታን በጥንታዊው ሥነ-ሕንፃ፣ በአስደናቂ የተፈጥሮ ገጸ በረከቶች  የተሞላች ናት፡፡

በረጅም ተራራዎች የተከበበችው ሀገሪቷ ለፈረስ ግልቢያ፣ ለእግር ጉዞ የተመቸች ስትሆን፣ በተራራዎች መካከል የሚገኙት ሀይቆቿ ለቱሪስቶች ማረፊያ ስፍራ ነው፡፡ ዱሻንቤ የታጂኪስታን  ዋና ከተማዋ ናት፣በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎችን አካታ የያዘችም ናት፡፡ ሩዳኪ የተሰኘው ፓርክ ደግሞ በብዙዎች የሚጎበኝና  የከተማዋ ዋና መገለጫም ነው፡፡

ሩዳኪ ፓርክ ፏፏቴዎችን እና ውብ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የተላበሰ የአትክልት ስፍራ አለው፡፡ ፓርኩ ካሉት የተፈጥሮ ገጸ በረከቶች ባለፈ በውስጡ እውቅ ሐውልትም ይዟል፡፡ ሀውልቱ መታሰቢያነቱ በ858 ዓ.ም በሀገሪቷ የበርካታ ሙያዎች ባለቤት ለነበረው ኢብኑ ሙሀመድ የቆመ ነው፡፡ኢብኑ ሙሀመድ ሙዚቀኛ፣ገጣሚ እና የጥንታዊ የፋርስ ስነ-ጽሁፍ መስራች ነበረ ግለሰብ ነው፡፡

የፋን ተራሮች በታጂኪስታን ከፍታ ላይ የሚገኝ የተራራ ስፍራ ነው፡፡ ተራራዎቹ ከ5000 ሜትሮች በላይ ከፍታ አላቸው። ሰንሰለታማ የሆነው ተራራው ቱሪስቶች የእግር ጉዞ ለማድረግ የሚመርጡት ሁነኛ ስፍራ ነው፡፡ በፋን ተራሮች ላይ በእግር የሚጓዙ እግረኞች በ2000 እና 4000 ሜትሮች መካከል ባሉ ከፍታዎች ላይ ጉዟቸውን ያደርጋሉ፡፡በተራራዎቹ መካከል የሚገኘው ሀይቅ ደግሞ ለስፍራው ተጨማሪ ውበትን የደረበለት ሲሆን ጎብኚዎች እረፍት ለማደረግ የሚመርጡት ስፍራ ነው፡፡

ጋርም-ቻሽማ የተፈጥሮ ፍልውሃ በታጂክ ቋንቋ ‹ትኩስ ምንጭ› የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ ከባህር ጠለል በላይ 2,325 ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ በጋርም-ቻሽማ ወንዝ መሃል ላይ ይገኛል። በተፈጥሮ ፍልውሃ የተከበበው ስፍራው የተላዩ ህብረ ቀለባትን የተላበሰ የመዋኛ ስፍራ አለው፡፡ ገንዳው 1.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን  35-45 ሜትር ስፋት አለው፡፡ ከመሬት በታች የሚወጣው የማዕድን ውሃ ከ 10 ሴ.ሜ እስከ 1.5 ሜትር ከፍታ ያላቸው ትናንሽ እና ትላልቅ ፏፏቴዎች መፍጠር ችሏል፡፡ ፏፏቴዎቹ አማካይ በሴኮንድ ከ 5 እስከ 7 ሊትር የሞቀ ውሃን ያመነጫሉ፡፡ብረት, አሉሚኒየም, ማግኒዥየም, ስትሮንቲየም, ፍሎራይን እና ሌሎች የኬሚካል ንጥረ ነገሮችን  ይዟል፡፡  

የውሃው ሙቀት በ 62 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ አካባቢ ነው፡፡ የፍል ውሃው ለቱሪስቶች የመዝናኛ እና ነፍስን ለማደስ ከመዋሉ ባሻገር ለአካባቢው ነዋሪዎች ምግብ ለማብሰልና ለመጠጥ የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን አካቶ ይዟል፡፡

የታጂኪስታን ብሔራዊ ሙዚየም በታጂኪስታን ሪፐብሊክ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ በዋና ከተማው የሚገኝ ግዙፍ ሙዚየም ነው፡፡ በማዕከላዊ እስያ የምትገኘውን ትንሿ የታጂኪስታ ሀገር ለመቃኘት የሚመጡ ጎብኚዎች ልዩ የሆነው የሙዚየሙ የኪነ ሕንፃ ዲዛይን ይደነቃሉ፡፡ የሙዚየው ጣሪያ የሀገሪቷን ብሔራዊ አርማ በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡

ሀገሪቷን ሲመሯቸው የነበሩ መሪዎችን ምስል፣ የተለያዩ ሀውልቶች፣ባለፈው ዘመን ህብረተሱ ሱጠቀምባቸው የነበሩ መሳሪያዎችን እና የአኗኗር ዜያቸውን የሚያሳዩ ቅርጻ ቅርጾች የያዘ ነው፡፡

በመዲናዋ ትልቁ የቱሪስት መስህብ ሲሆን ግዙፉ የዱሻንቤ ባንዲራ በዚህ እድሜ ጠገብ ሙዚየሙ አቅራቢያ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2023 ሙዚየሙ በ 100ሺ576 ቱሪስቶች የተጎበኘ ሲሆን፣ 5176 የውጭ  እና 95ሺ 400  የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ ከ1936 እስከ 1991 ሁለተኛዋ ትልቁ የታጂኪስታን ከተማ እና የሱድ ግዛት ዋና ከተማ ነበረች ኩጃንድ።

ኩጃንድ በመካከለኛው እስያ ከሚገኙት ጥንታዊ ከተሞች አንዷ ነች፣ ከፋርስ ኢምፓየር ጀምሮ ከ2,500 ዓመታት በላይ እንዳስቆጠረች መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እ.ኤ.አ. በ1644 እስከ 1656 በሙጋል ንጉሠ ነገሥት ሻህ ጃሃን የተገነባው መስጂዲ ጃሚ ለአመታት የሙጋል ንጉሠ ነገሥታት ንጉሠ ነገሥት መስጊድ ሆኖ አገልግሏል። መስኪዱ በውብ የኪነ ህንጻ ዲዛይኖች የተዋበ እና በውስጡም ሌሎች በርካታ ህንፃዎች አሉት ፡፡

የሻህ ጃሃን መስኪድ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለሃይማኖታዊ ስርዓት የሚገለገሉበት ስፍራ ነው፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

ሩሲያ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተፈፀመው የግድያ ሙከራ የባይደን አስተዳደር ስህተት ነው አለች

Next Post

የአልሸባብ ጥቃት በሶማሊያ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የአልሸባብ ጥቃት በሶማሊያ

የአልሸባብ ጥቃት በሶማሊያ

በድሬደዋ በደረሰ የመኪና አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

በድሬደዋ በደረሰ የመኪና አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አልፏል

ችግር የፈጠረው ብልሀት

ችግር የፈጠረው ብልሀት

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?