፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 08 2016| NBC ETHIOPIA-በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የ2024 የአውሮፓ እግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታን ሲከታተሉ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ቢያንስ ዘጠኝ የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ ።
ጥቃቱ የተፈጸመው መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ በማፈንዳት እንደነበር የሀገሪቱ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሙሀመድ የሱፍ ተናግረዋል ።
የሞቃዲሾ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት ከሟቾች በተጨማሪ ከ20 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ እንደተጠናቀቀ ከባድ አስፈሪ ፍንዳታ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
በሶማሊያ የደረሰውን ጥቃት የአልቃይዳ ክንፍ እንደሆነ የሚነገርለት እና በሀገሪቱ ከ17 ዓመታት በላይ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው አልሸባብ ሀላፊነቱን እንደወሰደ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












