፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 08 2016| NBC ETHIOPIA-በሀገራዊ ምክክር ዙሪያ በተለያዩ ተቋማት የተደረጉ ጥናቶች ሀገራዊ ምክክር በተለያዩ ምክንያቶች ሊደናቀፍ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡
በምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ተሞክሮዎች ላይ ቅኝት በማድረግ የተሰሩት እነዚህ ጥናቶች ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዳይሆንና እንዲደናቀፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ከዚህ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ይዘረዝራሉ፡፡
????በተለያዩ ቡድኖች መካከል እጅግ ሰፊ የሆነ የሀይል አለመመጣጠን ሲኖር እና የገነገኑ ሀይሎች (ቡድኖች) አቅማቸውን ተጠቅመው የሀገራዊ ምክክሩን አቅጣጫ የማስቀየር አዝማሚያ ሲያሳዩ፤
????በምክክር ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና ሊኖራቸው የሚችሉ ባለድርሻ አካላት በአግባቡ ተደራጅተው ሀሳባቸውን ማቅረብ ሳይችሉ ሲቀሩ፤
????አንዳንድ ባለድርሻ አካላት እና ቡድኖች በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ዝቅተኛ ተነሳሽነት ሲያሳዩ ወይም ጨርሶውኑ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ፤
????የምክክሩ ሂደት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ የግዜ ጫና ሲያጋጥም የሚሉት መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ኮሚሽን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












