፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 08 2016| NBC ETHIOPIA-ምስራቅ ጎጃም ዞን የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትዉልድ በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ችግኝ ተከላ ፕሮግራም እየተካሄደ ነዉ።
በደጀን ከተማ በተካሄደዉ ሁለተኛዉ ምእራፍ አንደኛዉ ዙር የአረንጓዴ አሻራ የማስጀመሪያ የችግኝ ተከላ በማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የምስራቅ ጎጃም ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑን ጨምሮ፣ የመከላከያ አመራሮች፣ የምስራቅ ጎጃም ከፍተኛ አመራሮች፣ የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የወረዳ አመራሮች፣ ከሁሉም ወረዳዎች የተዉጣጡ ወጣቶች፣ የአካባቢዉ አርሶ አደሮች በተከላ ፕሮግራም ተሳትፈዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ እንደገለጽት ቂምና ቁርሾን በመንቀል አንድነትን፣ ሰላምንና መፈቃቀርን የምናጸናበት የተከልናቸዉን ችግኞች በመንከባከብ የምናጸድቅበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም 215 ሚሊዮን ችግኝ የሚተከል ሲሆን በሚወጣዉ ፕሮግራም መሰረት በአንድ ቀን የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ 36.6 ሚሊዮን ለመትከል እንደታቀደ የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ መኮነን ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












