፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 08 2016| NBC ETHIOPIA-በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተፈፀመው የግድያ ሙከራ የባይደን አስተዳደር ስህተት ነው ስትል ሩሲያ ከሳለች፡፡
ከክሬምሊን ትናንት የወጣው መግለጫ እንደሚያሳየው በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ለመፎካከር የሚዘጋጅትን እጩ ዶናልድ ትራምፕን ለመግደል በተጠነሰሰው ሴራ የባይደን አስተዳደር በቀጥታ እጁ አለበት ተብሎ ባይታመንም ግን የአስተዳደሩ ባለስልጣናት ለዚህ መሰል ጥቃቶች የተመቻቹ መደላደል ይፈጥራሉ ነው ያለው ክሬምሊን፡፡ ትራምፕ በፔንሲልቫኒያ የምርጫ ቅስቀሳቸው ላይ እያሉ በተተኮሠባቸው ጥይት ጆሮአቸው ላይ መቁሰላቸው ይታወቃል፡፡

የግድያ ሙከራውን ያደረገው ሰው ደግሞ ወዲያውኑ በመገደሉ የተነሳ የጥቃቱን አላማና ከበስተጀርበው የማን እጅ እንዳለበት ለማወቅ ያለመቻሉ ነው የተገለፀው የክሬምሊን ባለስልጣናት በሰጡት ማብራራያ ትራምፕን ለመግደል በተቀነባበረው ሴራ የአሜሪካ የወቅቱ አስተዳደር ክፍተት እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












