፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 06 2016| NBC ETHIOPIA- የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ጥምረት (ኔቶ) አባላት ዩክሬንን ለመርዳት ፍላጎት የላቸውም ሲሉ የፖላንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራዶስላው ሲኮርስኪ ተናገሩ፡፡
ኬይቭ ጦርነቱን ማሸነፍ ትፈልጋለች ያሉት ሚኒስትሩ፤ አሜሪካ መራሹ ቡድን ዩክሬንን የኔቶ አባል እንድትሆን አለመፍቀዳቸው፤ በአባላቱ መካከል አለመግባባት እንዳለ አመላካች ነው ሲሉ ኔቶን ወቅሰዋል ፡፡
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ያለውን ጦርነት እንድታሸንፍ ከተፈለገ፤ ኔቶ የረዥም ጊዜ እርዳታ ለኬይቭ ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ ራዶስላው ሲኮርስኪ አሳስበዋል ሲል አር ቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












