፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 04 2016| NBC ETHIOPIA-“የዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ” በሚል ዩኒቨርሲቲዎች ማህበረሰቡን ሊያገለግሉበት በሚገባ ሃላፊነት ዙሪያ የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው።
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ሃገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግና ሳይንሳዊ አሰራሮችን ለማጎልበት ያግዛል ያለው በየወሩ የሚያዘጋጀው መድረክ አካል ነው።

አካዳሚው ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በትብብር ባዘጋጀው በዛሬው መድረክ ዩኒቨርሲቲዎች ህብረተሰቡን የማስተማር፣ ምርምር የማድረግና የማህበረሰብ አገልግሎት የመስጠት ሃላፊነት ቢኖርባቸውም ማህበረሰብን የማገልገል ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ አለመሆኑ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰሯቸው የምርምር ውጤቶች በሚፈለገው ልክ መሬት ወርደው ለህብረተሰቡ ጥቅም እየሰጡ አለመሆኑ በማሳያነት ቀርቧል።
በህብረተሰቡና በዩኒቨርስቲዎች መካከል የቅንጅት መላላት ለችግሩ አንዱ ምክንያት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የክትትልና ድጋፍ አናሳ መሆንም እንደተጨማሪ ምክንያት ተነስቷል።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












