፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 01 2016| NBC ETHIOPIA-የምዕራብ አፍሪካ ቀጠና የመከፋፈል አደጋ ተጋርጦበታል ሲል የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ አስታወቀ፡፡
ህብረቱ ይህን ያለው ስልጣንን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የያዙት ሶስት ሀገራት የራሳቸውን ጥምረት መፍጠራቸውን ተከትሎ ነው ፡፡

ቡርኪና ፋሶ ፤ ማሊና ኒጀር ከኢምፔራሊስቶች ነጻ የሆነ ማህበር መስርተናል ማለታቸውን ተከትሎ ነው ኢኮዋስ ይህንን መግለጫ ያወጣው ፡፡
የኢኮዋስ ሊቀመንበር ለ50 ዓመታት የቆየውን ህብረት አደጋ ላይ የሚጥል ጥምረት ነው በማለት ካወገዘ በኋላ፤ ሀገራቱ ውሳኔውን ካልቀለበሱት የሚመጣው ውጤት አስከፊ ነው ብሏል፡፡
ቡርኪና ፋሶ ፤ማሊና ኒጀር ባለፈው ቅዳሜ 15 አባላት ካሉት ኢኮዋስ ተገንጥለው የሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን የተባለ ጥምረት መመስረታቸው ይታወሳል ፡፡ ኢኮዋስ ጥምረቱ ለቀጠናው ሀገራት ሰላምና ደህንነትን የማያመጣ ነው ሲል አጥብቆም አውግዞታል ፡፡ ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












