፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 28 2016| NBC ETHIOPIA-የህዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ስራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እና ተቋማዊ ለውጦችን በማከናወን በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ እንደሚገኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በቀን 900 ፓስፖርት መስጠት የነበረውን አገልግሎት ወደ 1700 ማድረስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ቀደም ብለው የተጠራቀሙ ጥያቄዎችን አስተናግዶ ለመጨረስ በተሰራ ስራ 1 ሚሊዬን ፓስፓርት ታትሞ ገብቶ እስከ 87 በመቶ ተሰራጭቷል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተከማቹ ቅሬታዎች 100 በመቶ መፈታታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ 10 ሺ 467 ሰዎችን መመዝገብ የተቻለ መሆኑን በመግለጽ ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ 18 ሺ ሰዎች ቅጣት እንዲከፍሉ ተደርጓልም ነው ያሉት፡፡
በ88 ሀገሮች የቪዛ አገልግሎት በመክፈት ለ81,9278 ተስተናጋጆች e-visa ጨምሮ የቪዛ አገልግሎት መሰጠቱንም ጠቁመዋል፡፡
እንዲሁም ለ4,276,474 ግለሰቦች በአየርና በየብስ መዳረሻ ጣቢያዎች አገልግሎት ተሰጥቷል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
በአሁኑ ወቅትም ተቋሙን የዘመነ እና አገልግሎቱን በጥራት የሚሰጥ ተቋም ለማድረግ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












