፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 21 2016| NBC ETHIOPIA-የጣፋጭ ምግቦች በተለይም ደግሞ የአይስ ክሬም አብዝቶ ወዳጅ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡በውድ ይሸጣል ወደ ተባሉበትም ስፍራም አቅንተው በከፍተኛ ዋጋ ሊገዙት የተዘጋጁት ብሉኝ ብሉኝ የሚለው አይስክሬም ለመግዛት እና ለመመገብ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት፤ ከነፍሳት እንደሚዘጋጅ ቢሰሙ ምን ይሰማዎታል?
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ 2050 የአለም ህዝብን ለመመገብ የምግብ ምርት በእጥፍ መመረት እንደሚገባው ይህንን ግን ለማሳካት አዳጋች በመሆኑ ነፍሳትን እንደ አማራጭ የምግብ አይነት መጠቀም ከስጋት እንደሚታደግ ያወጣው ሪፖርት ያሳያል፡፡
ይህንን ሪፖርት ተከትሎ ይመስላል ታዲያ በደቡብ አፍሪካዊቷ መዲና ኬፕ ታውን የሚገኝ በፈረንጆቹ 2017 ጅማሮውን ያደረገው ጎርሜት ግሩብን የተሰኘ ተቋም ከነፍሳት የተዘጋጁ አይስክሬም ይዞ ብቅ ያለው::

ይህ የቅንጦት ምግቦችን የሚሸጠው ተቋም ከበረሀ ዝምቦች ከሚገኝ ኢንቶ ወተት እንዲሁም ከሌሎች ነፍሳት በሚገያገኛቸው ንጥረ ነገሮች ነው የተለያየ ጣዕም ያላቸውን አይስክሬሞችን የሚያቀርበው፤
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2019 ለመጀመሪያ ጊዜ ብቅ ያለውን አይስክሬም ባለቤት እና የድርጅቱ መስራች የሆነችው ሊሃ ቤሳ በምግብ ምርት እና አጠቃቀም ስርአት ውስጥ ለነፍሳት የሚሰጠውን ቦታ እንዲሁም የተሳሳተ አጠቃቀም መቀየር እንፈልጋለን ስትል ትናግራለች፡፡
ምንም እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ ከ2000 በላይ የሚሆኑ ነፍሳት ለምግብነት ቢውሉም በአብዛኛው በእስያ ባሉ ሀገራት በመሆኑ አሁንም ድረስ ወደ ምዕራባውያን የማዳረስ ስራ ላይ ሰፊ ክፍተት እንዳለ ይነገራል፡፡ሊሃ ስንጀምር ብዙ ተቃውሞዎች ይገጥመናል የሚል ግምት ነበረን ነገር ግን ሁሉም ሰው አይስክሬም ይወዳል፤ ስትል ለሲኤንኤን ተናግራለች::

የአይስ ክሬሞቹ ጣዕም ይበልጥ ተወዳጅ ለማድረግም የቸኮሌት፤ የኦጮሎኒ ቅቤ እና ሌሎች ምርቶችን በመጨመር ጠንከር የሚለውን ኢንቶ ወተት ያለውን ቃና እንዲጠፋ እናደርጋለን ስትል ትገልጻለች፡፡
ነገር ግን ድርጅቱ ከጣዕም ባሻገር በንጥረ ነገር ከፍተኛ ይዘት ባላቸው የነፍሳት ተዋፅኦዎች አይስክሬሙን እንደሚዘጋጅ የምትገልጸው ሊሃ በተለይም “ጥቁር ጠንከር ያለ ዝንብ ከበሬ ሥጋ ጋር የሚወዳደር ፕሮቲን እና የስብ ይዘት ያለው ሲሆን ዚንክ፣ ብረት እና ካልሲየም በውስጡ አሉት ትላለች፡፡
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጻም ነፍሳት ከስጋ እና ከአሳ የማይተናነስ ንጥረ ነገሮችን በውስጣቸው መያዛቸው ይናገራል፤የኢንሴክት ኢኮሎጂስቶች እንደሚገልጹት በተለይም ከነፍሳት የሚገኘው ወተት ከላክቶስ ፤ከግሉተን ስኳር ነጻ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡
ጎርሜነት ግሩብን የተሰኘው ተቋም ከአይስክሬም ባለፈ ሌሎች በነፍሳት የሚሰሩ ምግቦችንም በስፋት ይሸጣል፡፡መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመጪው ጊዜያት የነፍሳት ፍላጎት እጅጉን እየጨመረ እና ዋጋቸውም በዛው ልክ እያሻቀበ እንደሚሄድ ይጠቁማሉ፡፡የፈለገ ዋጋው ቢንር እና በቅንጡ ሆቴሎች ቢገኝ የሀገሬ ሰው እንደሚለው ባይበላስ ቢቀር ብለናል፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዩን












