፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 21 2016| NBC ETHIOPIA-የህዝብ ተወካዩች የምክር ቤት አባላት የተሳተፉበት የምክክር መድረክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።
የምክክር መድረክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ አፈ ጉባዔው አቶ ታገሰ ጫፎ የምክክር መድረኩ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አፈፃፀም፣ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ፣ አስተዳደራዊ ህግና የፌዴራል መንግሥት የመካከለኛ ጊዜ የኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የሚያተኩር እንደሆነ ጠቁመዋል።
እየተገባደደ ባለው በጀት አመት በተለይ በአዲስ አበባ በስኬት የተከናወነው የምክክር ኮሚሽን የአጀንዳ ማሰባሰብ ተግባር በክልሎችም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የታለመው ሀገራዊ መግባባት እውን ይሆን ዘንድ በክልሎችም ተመሳሳይ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ እያንዳንዱ ዜጋ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል።
በተመሳሳይ በሀገሪቱ ባለፉት ዘመናት ተደራራቢ እየሆኑ ለመጡት ቅራኔዎች እና ቁርሾዎች እልባት ያገኙ ዘንድ የሽግግር ፍትህ የፖሊሲ ማዕቀፍን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አመላክተዋል።

በፌደራል ደረጃ የተዘጋጀውና በሀገሪቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችላል የተባለው የአስተዳደራዊ ህግን ክልሎች ተግባራዊ እንዲያደርጉም ጥሪ ማቅረባቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












