፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 21 2016| NBC ETHIOPIA-ከመገናኛ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ከሃያት ሆስፒታል በኋላ ከነገ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለማንኛው ተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሰታወቀ።
መንገዱ ከነገ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ምሽትን ጨምሮ ለማንኛውም አይነት ተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሰታወቀ።
አሽከርካሪዎች ሆስፒታሉ ጋር ከመድረሳችው በፊት ያሉትን ቀኝ መታጠፊያዎችን በአማራጭነት እንዲጠቀሙ ገልጿል።
አዲስ አበባ ከተማን እንደስሟ ዉብና ምቹ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ካሉት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መካከል አንዱ የኮሊደር ልማት ስራ ነው። በመሆኑም ይህንን ስራ በአጭር ጊዜ አጠናቆ የትራፊክ እንቅስቃሴውን ምቹ ለማድረግና እንግልትን ለማሳጠር የተወሰኑ መንገዶች ዝግ ይደረጋሉ።
የከተማዋ ነዋሪዎች በልማት ስራው ምክንያት እየተፈጠሩ ላሉ ጊዜያዊ እንግልቶች ላሳዩት ትዕግስትና ትብብር ከልብ እናመሠግናለን ብሏል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












