፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 21 2016| NBC ETHIOPIA- በኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድምጽ መስጠት የጀመረ ሲሆን ህዝቡ በዋና ከተማይቱ ቴህራን እና ሌሎች ከተሞች ድምጽ ለመስጠት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በማቅናት ነው።
ባለፈው ወር ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ በሄሊኮፕተር አደጋ ከሞቱ በኋላ አራት እጩዎች – መሀመድ ባከር ቃሊባ ፣ ሰኢድ ጃሊሊ ፣ መስኡድ ፔዜሽኪያን እና ሙስጣፋ ፑርሞሃማዲ ለፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ።
በዘንድሮው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቢያንስ 64 ሚሊዮን የኢራን ህዝብ ድምጽ መስጠት ይችላል ተብሏል፡፡
በባህር ማዶ የሚኖሩ ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢራናውያንም በተለያዩ ሀገራት በተዘጋጁ 344 በተመረጡ የምርጫ ጣቢያዎች አርብ በሚካሄደውምርጫ ድምፃቸውን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው።የምርጫው ውጤት ቅዳሜ ይፋ እንደሚሆን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












