፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 20 2016| NBC ETHIOPIA-ኢትዮ ቴሌኮም “ስማርት ካምፓስ ለትምህርት ልህቀት” በሚል መሪቃል በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ በስድስት ኪሎ ጊቢ የስማርት ካምፓስ የማስጀመሪያ መርሀግብሩን አካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ኢትዮጵያ እያደረገችው ለሚገኘው የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ በትምህርት ዘርፋ የስማርት ካምፓስ ጅማሮ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል።
ስማርት ካምፓስ አገልግሎት ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን በቀላሉ ለማገናኘት እና የሚሰጠውን አገልግሎት ከማዘመን ባለፈ ለትምህርት ጥራት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም አንዱ አገልግሎት በሆነው ቴሌብር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን እና በመጪው ጊዜያት የአዲስአበባ ዮኒቨርሲቲ የክፍያ ስርአቱን ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል ለማድረግ ሰፊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል ።
ኢትዮ ቴሌኮም እና አዲስአበባ ዮኒቨርስቲ Smart campus for Acadamic excellence እና የጥቁር አንበሳ የክፍያ ስርአት በቴሌብር ለመደገፍ የሚያስችሉ ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
በ -የአብስራ ሚሊዮን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












