፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 18 2016| NBC ETHIOPIA- በተለያዩ ጊዜያት ለጆራችን እንግዳ እና አጃይብ የሚያስብሉ ጉዳዮች ከተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰማለን ፡፡በየጊዜው በምድራችን ላይ ያልተለመዱ ለየት ያሉ ሁነቶች ሲከሰቱ በድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ከሰሞኑም የሶስት አመቱ ዴንማርካዊው ውሻን የአለማች ረጅሙ ህያው ውሻ በማለት የተለያዩ አስገራሚ ነገሮችን በመመዝገብ የሚታወቀው ጊነስ ወርልድ ሪከርድስ በድንቃድንድ መዝገቡ ከትቦታል፡፡
ከስድስት ወራት በፊት በሳምባ ምች ህይወቱ ያለፈውና 1.046 ሜትር ቁመት በነበረው አሜሪካዊው ዜኡስ ተይዞ የነበረው የአለማችን ትልቅ ውሻ የሚለውን ማዕረግ ኬቨን መረከቡን ጊነስ ዎርልድ እወቁልኝ ብሏል፡፡
የአለማችን ረጅም ውሻ የሚል ማዕረግን ከጊነስ ወርልድ ማግኘት የቻለው ኬቨን በርዝመቱ ብቻ ሳይሆን በድርጊቶቹም የተለየ መሆኑን ነው ባለቤቶቹ የሚናገሩት፡፡
ኬቨን በአሜሪካ ዌስት ዴስ ሞይን አዮዋ ከሚወዳቸው ባለቤቶቹ ትሬሲ እና ሮጀር ዎልፍ ፤ ከልጆቻቸው እንዲሁም ከበርካታ ሌሎች እንስሳቶች ጋር ይኖራል፡፡ ኬቨን የተሰኘው ይህ ውሻ 0.97 ሜትር ወይም 3 ጫማ ከ2 ኢንች ርዝማኔ ያለው ሲሆን ይህም የሶስት አመት ልጅ አማካይ ቁመት እንደማለት ነው፡፡
ኬቨን የዓለማችን ረጅሙ ወንድ ውሻ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ማለት በቤት ውስጥ ብቻውን ለመተው በቂ ነው ማለት አይደለም ይላል ጊኒየስ ብክ በክታቡ፡፡
ለወትሮው ውሾች በሀይለኝነታቸውና በደፋርነታቸው የሚታወቁ ቢሆኑም ኬቨን ግን የእነዚህ ተቃራኒ ነው፡፡ ውሾች የቤት ጠባቂዎች እንደሆኑ በበርካቶች ይታመናል ኬቨር ግን ተባቂ ይሻል ፡፡ በጭራሽ በቤት ውስጥ ብቻውን መሆን የማይችንና ፈሪም ጭምር ነው፡፡ ኬቪን ብዙ ነገሮችን ይፈራል በተለይ የቤት ውስጥ ማፅጃ ቫኪውም በጣም ይፈራል ከሱ ለመሸሽ ዘሎ ይሮጣል ትላች አሳዳጊው ትሬሳ፡፡በቤት ውስጥ ሰው ከሌለ ይጮሃል ያለቅሳል፡፡

ባለቤቶቹ እደሚሉት ከሆነ ኬቨን የጊነስ ወርልድ ባለሙያዎች ቁመቱን ለመለካት በመጡ ጊዜ አስቸግሮ ነበር፡፡ይህ ውሻ አብዛኛውን ጊዜ ሶፋ ላይ አልያም አልጋ ላይ በመተኛት ያሳልፋል፡፡ እንዲያውም አንድ ሰው በስህተት በሚወዳት ቦታው ላይ ከተቀመጠ ይጮሃል ስትል ትሬሳ ትናገራለች፡፡
የኬቪን ተወዳጅ ተግባር እንቅልፍ መተኛት ነው። ሶፋውን ላይ በመውጣት ለረጅም ሰአታት መተኛት የእሱ ተወዳጅ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ነው፡፡
ኬቪን ቀልደኛ ነው እና እጅግ በጣም ተግባቢ ነው፡፡ እሱ በሚኖርበት ጊዜ ሁሉም ሰው ደስተኛ ነው ሁሉም ሰው እሱን ማየት ይወዳል፡፡ ከኩሽና መደርደሪያ ላይ ምግብ ይሰርቃል ከዚህ መጥፎ ተግባሩ ውጭ ጥሩ ባህሪ አለው ፡፡ምንም እንኳን ሰነፍ ቢሆንም ጥሩ ባህሪ ያለው ነው፡፡
በእንስሳት ሕክምና ክሊኒክ ውስጥ የምትሠራው ትሬሲ ኬቨን በየቀኑ ከስድስት እስከ 10 ኩባያ ምግብ እንደሚመገብም ነው የምትናገረው፡፡ በእሱ እድሜ ካሉት ውሾች በሚያደርነው ነገር የተለየ መሆኑም ትገልፃለች፡
በክፍል ውስጥ ካሉት እንስሳት ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ የሚያውቅ አይመስለኝም፤ ያለማቋረጥ ወደ ትናንሽ አልጋዎች ለመጫወት እና ትናንሽ ውሾች የሚያደርጉትን ሁሉ ለማድረግ ይሞክራል ትላለች፡፡
በሄደበት ሁሉ ብዙ ትኩረትን የሚያገኘው ኬቨን ብዙ ሰዎች በትልቅነቱን የተነሳ ፈረስ አድርገው ያስባሉ አንዳንዶቹም ፈረስ ነው እያሉ እንደሚጠይቁም ነው አሳዳጊዎቹ የሚናገሩት፡፡ አለፍ ሲልም ኮርቻ አድርገው ሊጋልቡት እንደሚችሉ በቀልድ መልክ ይናገራሉ ስትል ትሬሲ ትገልፃለች፡፡
ከቤተሰቦቹ ጋር በጣም ቅርበት ያለው ሲሆን በተለይ ከልጆቹ ጋር የተለየ ፍቅር እና ቀረቤታም አለው፡፡ ኬቨንን የዓለማችን ረጅሙ ውሻ ሆኖ በይፋ መመዝገቡ ለቤተሰባችን አስደሳች ነው ስትል ትሬሳ ትናገራለች፡፡












