፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 15 2016| NBC ETHIOPIA-እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ጦርነት የሚያስቆም ማንኛውም ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል በሬ ክፍት ነው ሲል ሀማስ አስታወቀ፡፡
የሀማሱ መሪ ኢስማኤል ሀኒያህ የፍልስጤምን ፍላጎት ባሟላ መልኩ የሚደረግ የትኛውንም ድርድር ቡድናቸው በቅንነት እንደሚቀበለው ገልጻዋል፡፡
ቴላቪቭ በጋዛ ህዝብ የምታካሄደውን የዘር ማጥፋት ጦርነት ማቆም እንዳለባት ቤሩት ላይ በነበራቸው ስብሰባ የተናገሩት ሀኒያህ ፤ ዘላቂ ተኩስ ማቆምን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለውይይት ተዘጋጅተዋል፡፡ ሀኒያህ ይህንን ይበሉ እንጂ ከእስራኤል ባለስልጣናት ስለድርድሩ ቅድመ ሁኔታ እስካሁን የተሰጠ ምላሽ የለም ፡፡ ዘገባው የቲ አር ቲ ወርልድ ነው
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












