፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 14 2016| NBC ETHIOPIA- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ክላቨር ጋቴት ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ኢትዮጵያ በመጭው ሀምሌ ወር የምታስተናግደውን 4ኛዉ ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግና በጋራ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ መሆኑን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቀጣይ መስከረም ወር በኒውዮርክ በሚካሄደው የመጭው ዘመን ስብሰባ (Summit of the Future) ላይ ሊኖሩ በሚገባቸው ተሳትፎዎች ዙሪያም የሀሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ አመላክቷል፡፡
አፍሪካ አዳራሽ የተሰኘውን የኮሚሽኑ አዳራሽ የእድሳት ስራ በአዲስ አበባ እየተከናወነ ከሚገኘው የኮሪደር ልማትና ከተገነቡት የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ጋር በማስተሳሰር አዳራሹን አንድ የቱሪስት መስህብ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር መደረጉ ተገልፅዋል፡፡
በተጨማሪም ኮሚሽኑና ኢትዮጵያ በልማትና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተባብረው መስራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












