Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

በፈረንጆቹ 2024 ለኑሮ ውድ የሆኑ ከተሞች

June 19, 2024
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | ሰኔ12 2016| NBC ETHIOPIA- በርካቶች የሀብት ማማ ተቆናጠው ኑሮን ሲያጣጥሙ ብዙሃኑ ደግሞ ከድህነት ወለል በታች በስቃይ ኑሮን ይገፋል።ይህ የዓለም ሁለት ገጽታ ነው፡፡ ድህነት ያስመመረራቸው የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ሀብታም ወደሚባሉት ወደተለያዩ የአለም አገራት ያቀናሉ፡፡ አገራትም በየዓመቱ ባላቸው የምጣኔ ሀብታዊ እድገት መሰረት ለኑሮ ውድ እና ርካሽ ተብለው ደረጃ ይወጣለቸዋል።

ታዲያ ከሰሞኑም ሜርሴር የኑሮ ዋጋ ዳሰሳ ባደረገው ጥናት መሰረት በየዓመቱ በዓለም ላይ የኑሮ ውድነት የሚስተዋልባቸውን እና በአንጻሩ ደግሞ ለመኖር ርካሽ የሆኑ ከተሞችን በጥናት ላይ ተመስርቶ ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል።

የዚህ ዓመቱ ጥናት በ226 የዓለማችን ከተሞች ላይ የተደረገ ሲሆን መሰረታዊ የሚባሉ የኑሮ ጥያቄዎችን መነሻ አድርጎ ስለመከናወኑ ተገልጿል።

በሪፖርቱም መሰረት የአካባቢው መጓጓዣ፣ ምግብ፣ አልባሳት፣ የቤት እቃዎች እንዲሁም መዝናኛዎች ጨምሮ ከ200 በላይ ዕቃዎችን በማነፃፀር የዋጋ ሁኔታን ታሳቢ አድርጓል ተብሏል።   

በጥናቱም መሰረትም ሆንግ ኮንግ በፈረንጆቹ 2024 ለውጭ አገር ሠራተኞች በጣም ውድ ከተማ ሆናለች፡፡ ከተማዋ ከዚህ በፊት በተደረገ ጥናትም ለውጭ አገር ሠራተኞች ውድ ከተማ የነበረች ሲሆን ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ይላል ጥናቱ፡፡

Hong Kong Island from Kowloon.

እ.ኤ.አ. በ2022 እና 2023 አመታዊ ዝርዝር ቀዳሚ የነበረችው የእስያ ከተማ፣ ሲንጋፖር ሆንግ ኮንግ በመከተል በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የስዊዘርላንድ ከተሞች የተቀሩትን ደረጃዎች የያዙ ሲሆን ዙሪክ፣ ጄኔቫ፣ ባዝል እና በርን እንደ ቅደም ተከተላቸው ከሶስተኛ፣ እስከ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ኒውዮርክ ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ውዷ የአሜሪካ ከተማ ስትሆን የእንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ደግሞ ባለፈው አመት ከነበረችበት የ17ኛ ደረጃ ወደ ስምንተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች ተብሏል። ናሶ፣ ባሃማስ ዘጠነኛ ደረጃን የያዘች ሲሆን ሎስ አንጀለስ 10ኛ መሆን ችላለች።

በሪፖርቱ መረጃ መሰረት በተለይ በከፍተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጡ ከተሞች የኑሮ ውድነት እንዲጨምር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል ውድ የቤት ገበያ ፣ የትራንስፖርት፣ የእቃ እና የአገልግሎት ዋጋ መጨመር ናቸው።

በከተማ ደረጃ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ በዋናነት የመኖሪያ ቤት ዋጋን መሰረት አድርጓል ሲል ጥናቱ አመላክቷል።በዚሁም መሰረት ከተሞች ባላቸው የቤት ኪራይ ዋጋ ከፍተኝነት ምክንያት የውጭ አገር ሰራተኞች  ከገቢያቸው ከፍተኛ መጠን ያለውን ለኪራይ ስለሚያውሉት ለሎሎች ወጪዎች የሚቀራቸው ገንዘብ አነስተኛ ስለመሆኑም በጥናቱ ተመላክቷል፡፡

በፈረንጆቹ 2023 እና 2024 መካከል፣ በአለም ዙሪያ የመኖሪያ ቤት ዋጋ  ብዙ ተለዋዋጭነት የነበረው እንደሆነ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በከተሞች መካከል በእጅጉ መለያየቱን ሪፖርቱ አመልክቷል።።

በተጨማሪም የዋጋ ግሽበት እና የምንዛሪ ተመን መዋዠቅ በአለም አቀፍ ሰራተኞች ደመወዝ እና ቁጠባ ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ማሳደሩ ተጠቁሟል።

ይፋ የተደረገው ዝርዝሩ ካለፈው ዓመት አገራቱ ደረጃ ጋር ሲነጻጸር ብዙ መቀያየሮችን ያሳየነው ተብሏል።ጥናቱ በፈረንጆቹ 2024 በአሜሪካ ያለው የኑሮ ውድነት በጉልህ ያሳየ ነው ተብሏል። ሰባት የአሜሪካ ከተሞች በውድነት እስከ 20 ባለው ደረጃዎች ውስጥ ተካተዋል።

በኑሮ ውድነት ዝቅተኛውን ደረጃ ወይንም ለወጭ አገር ሰራተኞች ለመኖር ቀላል ከሆኑት መካከል የፓኪስታን ከተማ ኢስላማባድ እና የናይጄሪያ ሌጎስ እና አቡጃ ይገኙበታል፡፡ሆኖም፣ ይህ በከፊል “የምንዛሪ ዋጋ በመቀነሱ” የተከሰተ ነው ተብሏል።

በየከተሞቹ ያለውን የኑሮ ውድነት ደረጃ ሲለይ ግምት ውስጥ ከገቡት 200 ምርቶች መካከል እንቁላል፣ የወይራ ዘይት እና ቡና ዋጋ ተጠቃሽ ተደርገዋል።የኑሮ ውድነት ተግዳሮቶች በዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና በሰራተኞቻቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል ሲል የሜርሴር የኑሮ ዋጋ ዳሰሳ ጥናት አመላክቷል ሲል ሲ ኤን ኤን ይዞት በወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

በ-ሀይማኖት ወርቁ

ShareTweetShare
Previous Post

የፍትህ ሚኒስቴር ልዑክ ቡድን ከብሪክስ አባል ሃገራት ከሆኑ የአቃቤ ሕግ አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው

Next Post

ሲሪል ራማፎሳ ቃለ መሀላ ፈጸሙ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
16
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post
ሲሪል ራማፎሳ ቃለ መሀላ ፈጸሙ

ሲሪል ራማፎሳ ቃለ መሀላ ፈጸሙ

ትላልቅ የምሽት ገበያዎች ያሉባቸው ሀገራት

ትላልቅ የምሽት ገበያዎች ያሉባቸው ሀገራት

አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?