፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤቱ በ2014 በጀት አመት በዋና ኦዲተር በኦዲት ግኝት መሰረት ብር ተመላሽ እንዲያደርጉ አስተያየት የተሰጠባቸውና ተመላሽ ያላደረጉ ተቋማት ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ ገልጿል።
ተመላሽ መደረግ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ ተመላሽ የተደረገው 11 በመቶ ብቻ መሆኑ ተገቢ አለመሆኑን የምክር ቤት አባላት ጠቁመ፤ ችግሮቹን መመርመር፣ በቀጣይም ገንዘቡን የማስመለስና ተጠያቂነትንም ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
የፌደራል ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ ሪፓርቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት 92 መስሪያ ቤቶች በኦዲት ግኝት መሰረት ተመላሽ እንዲያደርጉ ተብሎ አስተያየት ከተሰጠበት ብር 443,023,846.91 እና 23,055.00 ዶላር ውስጥ ተመላሽ የተደረገው ብር 48,217,965.67 ብር ብቻ መሆኑንና አፈጻፀሙም 11 በመቶ ብቻ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በባለበጀት መስሪያ ቤቶች በኩል እርምጃ እስከመውሰድ የሚደርስ መሻሻሎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ ነገር ግን ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት ግኝት እና ብር ተመላሽ ያላደረጉ መስሪያ ቤቶች ላይ ምክር ቤቱ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












