፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 07 2016| NBC ETHIOPIA- በኢትዮጵያ የግብርናውን ዘርፍ ለማዳሳደግ ባለሀብቶች በዘርፉ መዋለ ንዋይ ፈሰስ እንዲያደርጉ መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት ባለሀብቶች መሬት በመውሰድ ኢንቨስት እያደረጉ ይገኛል ። በሀገሪቱ ባለፉት አመታት 2.1 ሚሊየን ሄክታር በኢንቨስትመንት መወሰዱ የተገለፀ ሲሆን 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታሩ በሀገር ውሰጥ ባለሀብቶች የተያዘ ሲሆን 494ሺ በውጭ ባለሀብቶች መያዙን ግብርና ሚኒስቴር ገልጿል።
በክልሎች ለግብርና ኢንቨስትመንት ከተወሰደ መሬት 51 በመቶ እንዳለማ ተጠቁሟል ።በተለይ በጋምቤላ እና ቤንሻንጉልጉሙዝ ክልሎች ችግሩ የጎላ መሆኑ ተመላክቷል ።
የግብርና ሚኒስቴር እና ልማት ባንክ በጋራ በመሆን በግብርና ኢንቨስትመንት ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ምክክር እያደረጉ ይገኛል ። የብድር አቅርቦት ፣ በሚመለከታቸው አካላት የክትትል እና ድጋፍ አለመኖር ፣ ዝቅተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለዘርፉ እድገት ማነቆ መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












