፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 30 2016| NBC ETHIOPIA-ሩሲያ ሉዓላዊነቴን በመጣስና ወታደራዊ መረጃዎችን ለፈረንሳይ ሲያቀብል ደርሼበታለሁ ያለችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች፡፡
የፈረንሳይ ዜጋ ነው የተባለው ግለሰብ የወታደራዊ ተቋማትንና መሪዎችን መረጃ ለብዙ ዓመታት በድብቅ ሲሰልል እንደነበር የክሬምሊን ባለስልጣናት ተናግረዋል ፡፡

የሞስኮ የመረጃ ኮሚቴ የግለሰቡን ስም ባይጠቅስም ፤ ግለሰቡ ወደ ሩሲያ ለብዙ ጊዜ ሲመላለስ እንደነበርና ከሩሲያ ዜጎች ጋር በተለያዩ ሀገራዊ ስብሰባዎች በመገኘት በምስጢር መረጃ ሲያሾልክ እንደቆየ ገልጿል፡፡ ዘገባው የሞስኮ ታይምስ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












