፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት29 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሦስተኛ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት 1፡00 ሰዓት ከሜዳው ውጪ ከጊኒ ቢሳው ጋር ያደርጋል።
-በኢትዮጵያ ምድብ የሚኙትን ሴራሊዮን እና ጅቡቲን ትላንት ምሽት ያገናኘው የምድብ አንድ ሦስተኛ ጨዋታ በሴራሊዮን 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
-አርሰናል ቤልጂየማዊውን የኤቨርተን አማካኝ አማዱ ኦናና ለማዘዋወር ከክለቡ ጋር ንግግር መጀመሩ ተሰምቷል።
-የቼልሲ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ክለባቸው የሌስተር ሲቲውን አማካኝ ኬራን ደውስበሪ-ሆል እንዲያስፈርምላቸው ይፈልጋሉ።
-ጄምስ ማዲሰን በ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ከሚሳተፈው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ዉጭ ሆኗል።
-ዩክሬናዊው የከባድ ሚዛን ቡጢኛ ኦሌክሳንደር ኡሲክ ወደ ክሩዘር ሚዛን ውድድር እንደሚመለስ አስታውቋል።
-የወቅቱ የከባድ ሚዛን አንዲስፒዩትድ ሻምፒዮናው ኡሲክ በታህሳስ ወር ከታይሰን ፊዩሪ ጋር ከሚያደርጉት የድጋሜ ፍልሚያ በኋላ ወደ ክሩዘር ሚዛን ይመለሳል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












