፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 24 2016| NBC ETHIOPIA-የስልጣኔ ነጸብራቅ ናቸው የኪነ-ህንጻ ጥበቦች የኪነ-ህንጻ ጥበቦች ባላቸው ለየት ያለ ንድፍ እና በሚያስተላልፉት መልዕክት የሀገራት ምልክት በመሆንም ያገለግላሉ፡፡
በዛሬ ምርጥ አምስት የኪነ -ህንጻ ጥበብ ሲነሳ አብረው የሚነሱ የዓለም ምርጥ አምስት የኪነ-ህንጻ ጥበብ ባለቤቶችን ልናስቃኛችሁ ወደድን ፡፡
1.አርክቴክት ኖረማን ፎስተር
በአለማችን ላይ ያሉ የህንጻ ኪነ-ጠበብቶች ሲነሱ በግንባር ቀደምትነት የሚነሳው እንግሊዛዊው አርክቴክት ኖረማን ፎስተር ነው፡፡

ባበረከታቸው ቀለል ባሉ ዘመናዊ ንድፎቹ አለም አቀፍ እውቅና ተችሮታል፡፡ በሚሰራቸው ንድፎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማካተቱ የቴክኖሎጂው ጀግና የሚል ቅጽል ስም ባለቤት መሆን ችሏል፡፡
በ1967 ፎርሰት ፕላስ ፓርትነር በሚል ያቋቋመው የኪነህንጻ ማዕከል ባለፉት አራት አስርት አመታት ከ 500 በላይ ሽልማቶች እና እውቅናዎችን እንዲያገኝ አብቅተውታል፡፡
በ2002 የተገነባው የለንደን ከተማ አዳራሽ፣ በለንደን የሚገኘው ታዋቂው ዘ ጌርኪን ህንጻ እውቅናን ከለገሱት ስራዎቹ ጥቂቶች ናቸው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ 23 ከመቶ ብቻ ሴት የስነ ህንጻ ባለሞያ ወይም አርክቴክት እንዳለ ይነገራል፡፡
2. አርክቴክት ዛሃ ሃዲድን
ታዲያ በዚ በርካታ ሴቶች ባልደፈሩትነ የስነ- ህንጻ ጥበብ ላይ ጉልህ አስተዋጾዋን ያሳረፈቸው ታዋቂዋን ኢራቃዊት አርክቴክት ዛሃ ሃዲድን እናገኛታለን፡፡

እ.ኤ.አ 1993 የመጀመሪያ ስራዋ የሆነውን በጀርመን ከሚገኝ የእሳት አደጋ ማዕከልን ጀምሮ በርካታ አድናቆትን ያተረፉ የስነ ህንጻ ስራዎችን በተለያየ ጊዜ አበርክታለች፡፡ እስካሁን ድረስም በ44 ሀገራት ከ950 በላይ ህንጻዎችን ሰርታለች፡፡ ከስራዎቿ መሀል በአዛርባጃን የሚገኘው የባህል ማዕከል በ 2014 የለንደን ዲዛይን ሙዚየም ሽልማትን ሊያገኝ ችሏል፡፡ በአቡዳቢ የሚገኘው የሼክ ዛይድ ድልድይ ፣ በቤጂንግ የጋላክሲ ህንጻን ጨምሮ በርካታ የስነ-ህንጻ ዲዛይኖችን አበርክታለች፡፡ በሞያው አንቱ ለተባሉ ሰዎች የሚሰጠውን Pritzker Architecture ሽልማትን በመውሰድ የመጀመሪያዋ ሴት መሆን ችላለች፡፡
3.አርክቴክት ፣ ዲዛይነር እና ፀሀፊ ሊኮርቢዘር
በሶስተኛነት የምናገኘው ደግሞ ትውልደ ስዊዘርላንዳዊው አንጋፋ አርክቴክት ፣ ዲዛይነር እና ፀሀፊ ሊኮርቢዘር ነው ።

ሊኮርቢዘር በአሁን ወቅት ላለው ዘመናዊ የስነ ህንፃ ጥበብ ፈር ቀዳጆች ከሚባሉት አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል።
በአውሮፓ፣ አሜሪካ፣ በጃፓን እንዲሁም በህንድ አምስት ክፍለ ዘመናትን የተሻገሩ ስራዎችን ማበርከት ችሏል። እ.ኤ.አ በ2016 በተለያዩ ሰባት ሀገራት የሰራቸው 17 የስነ-ህንፃ ስራዎች ለዘርፉ ዘመናዊነት የላቀ አስተዋፅዖ በማድረጋቸው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት unesco የክብር መዝገብ ላይ አርፈዋል።
4.አርክቴክት ፍራንክ ጌህሪ
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተፈላጊ ከሆኑ አርክቴክቸሮች መካከል አንዱ ስለሆነው ፍራንክ ጌህሪ እንገራችሁ…

የሚሰራቸው ህንጻዎች አድናቆትን ከማምጣት ተሻግረው የግል መኖሪያ ቤቱ ሳይቀር የቱሪስት መስብ መሆን ችሎል፡፡ በስፔን የሚገኘው ጉገንሃይም ሙዚየም ፣ ማራኪ የህንጻ ጥበብ የታየበት ታዋቂው የዲዝኒ ኮንሰርት አዳራሽ እና በፈረንሳይ የሚገኘው የታዋቂው ሉኢስ ቩቶን ፋውዴሽን የምስረታ ህንጻ ከሰራቸውና እውቅናን ካስገኙለት ዲዛይኖች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
5.አርክቴክት ጸሀፊ እና መምህር የሆነው ፍራንክ ሎይድ
በርካቶች እስከዛሬ ከነበሩ የኪነ ህንጻ ጠበብቶች አቻ ያልተገኘለት እያሉ ያሞካሹታል ፡፡ የጥምር ሞያዎች ባለቤት የሆነውን አሜሪካዊው አርክቴክቸር ፣ ጸሀፊ እና መምህር የሆነው ፍራንክ ሎይድ ፡፡

ከዚህ አለም በሞት እስከ ተለየበት ጊዜ ድረስ በ70 አመታት የኪነ ህንጻ ስራ ጉዞው ከ 1ሺ በላይ ፈጠራ የተሞላባቸውን ህንጻዎች ሰርቷል፡፡ ለሃኛው ክፍለ ዘመን የኪነ ህንጻ ጥበብ ንቅናቄ ቁልፍ ሚናም እንደተጫወተም ይነገርላታል፡፡
በ-የአብስራ ብርሃኑ












