፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 21 2016| NBC ETHIOPIA-ኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምክክር ምዕራፍ የመክፈቻ መርሃግብር አካሄዷል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ህዝቡ በተወካዮቹ አማካኝነት የሚያነሷቸውን ጥያቄ ወደ ሀገራዊ ምክክሩ የሚያቀርቡበት ነው ብለዋል፡፡


ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮችን መፍትሄ ለመስጠት ወደ ጠረጴዛ በማምጣት ሰላምና ጠንካራ ሀገራዊ መንግስት ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡
ከሰዓት ጀምሮ ከአዲስ አበባ የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ለምክክሩ የሚረዱ ሃሳቦችን ያቀርባሉ፡፡


በመርሃ ግብር የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች በምክክርና በውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን ከማቅረብ በተጨማሪ ለሚነሱ ጉዳዮች የመፍትሄ ሃሳቦች ማመላከትንም ያካትታል፡፡
በመርሐግብሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ ተሳታፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት እና የመንግስት አካላት እና የተለያዩ ተቋማትና ማህበራት ተወካዮች ይመካከራሉ፡፡
በ- ሰላም ይልማ
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












