፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ግንቦት 19 2016| NBC ETHIOPIA- ደቡብ ኮርያ፣ ጃፓንና ቻይና፤ ሰሜን ኮርያ የኮርያ ልሳነ ምድር ሰላም እና መረጋጋት እንዳይኖረው እያደረገች ነው ሲሉ መውቀሳቸው ተገለጸ፡፡
ሶስቱ ሀገራት ከአምስት ዓመት በኋላ የመጀመሪያውን ስብሰባ ባደረጉበት ጊዜ በኮርያ ልሳነ ምድር ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር የጋራ ፍላጎታቸው እንደሆነ ተነጋግረዋል ተብሏል ፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፋሚዮ ኪሺዳ የሰሜን ኮርያን የኑክሌር መርሀ ግብር ማስቆም ለቀጠናው ሰላም መሆን አስፈላጊ እንደሆነና ይህንንም በጋራ ለመካለካል ሀላፊነት መውሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በኮርያ ልሳነ ምድር እየተካረረ የመጣውን ውጥረት ለማርገብ በአብሮነት በመቆም ፤ ቀጠናውን ማረጋጋት እንደሚገባ እና የሶስትዮሽ ትብብር ማድረግ ለሀገራቱ የጋራ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የሶስቱ ሀገራት ተወካዮች በውይይታቸው ወቅት ማንሳታቸው ታውቋል ፡፡ ዘገባው ቲ አር ቲ ወርልድ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












